Wednesday, January 8, 2020

የስልጤ በክልል መደራጀት አስፈለጊነት

የስልጤ በክልል መደራጀት ለምን አስፈለገ

1 ከአገልግሎት ተደራሽነት ይልቅ የበጀት ክፍፍልን መሠረት ያደረገ አስተዳደራዊ መዋቅር መኖር፣

2 በክልሉ የአስተዳደር መዋቅር ፍትሐዊነት የጎደለው የፖለቲካ ውክልና፣

3 የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊ ትስስርና ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው ማኅበረሰብ መፍጠር የሚያስችል የመሠረተ ልማት ትስስር አለመኖር፣

4 ዞኖች የክልል መቀመጫ ተደርጎ በሚመረጥበት ከተማ ላይ ከሚኖራቸው የሀብት ፈሰስ ጋር በተያያዘ የባለቤትነት ሕጋዊ ማዕቀፍ አለመኖር፣

5 የፖለቲካ ምኅዳሩ አሳታፊነት የጎደለውና አግላይ የፉክክር ፖለቲካ መሠረት መያዙ፡

Wednesday, February 27, 2019

መህማቾት

#መህማቾት_መሮሼ_ዚጠኜ
1) ሂመይ ታለ ወይ ባለ ደረሳይ።
2) ሁልም ግዝ ያቆምሳነይ ተፈይነትን።
3) ሁል ወለበ፥ ላመ ማ አለበ።
4) ለመጥከ እረውጣን ሰበ እቀድመያን ኤለ።
5) ገዋነ የሼዙይ ግነ አተ በሄ ምነ ጠቀልካሀ እላን።
6) ገደሞ የሰረርትም ለሰረርት በደችመ ትቃናት።
7) ገገ አቴነሴ ስሀረ ተስኮት ገገ አኬረሴ ጤብሰ እንደሮት እጠቅላን።
8) ገገከ ለላቀተለ አቴሀማት፥ ተዞፍከ ኤማት።
9) ለቄነጡኝ አዘር ደም ወጣኝ ባት ባሊ።
10) ገንደ በደል ዬለ በደል ታገቤሽ ባለ ማረቆ።
‘ገንዳ’ በሆድ የሌለን በሆድ ታገቢያለሽ (አለ ማረቆ)። (ማረቆዎች ስልጤን ገንዳ
ብለው ይጠሩታል፤ እንድንጠራጠር አደረጋችሁ ለማለት ነው።)
11) ለደልዋ ሎልድ የከሼ ግዘ ሁለ እሎቡይ።
12) ዱዱቆ፥ ነይ ሞቆ።
13) ለዱሬሸ ብቼ፥ ዜገ ተጎነኔከ በቼ፥
14) ለዱንየ ተዮን ላያንዋ ለበረከ የብኪ።
15) ዶንቀ ምሽት ያለይ ሚሽ ባብሌ እላመሽ።
16) ጀማሽ ያላን በለ፥ ሳፍራሽ ቀልቀለ።
17) ጅረዋ አማቺ በሩቅን ፈየ
18) ለጭልማይ ኑር፥ ለምካትሚ መለ ያትኬሺማን።
19) ዱሬሻም ዜጋም ቅጦም እበኮን።
20) ሀብታምም ድኻም እኩል ያለቅሳሉ።
21) ዱበን ባለቢ ኤት አመረዋ ወራበ እለትቀበጥ።
22) ዱንየ ላማድ፥ ኡምር ለተውበት።
23) ሊመርጥ የመጠ ቢጦቅሱይ እለትመረር
24) ሊሌቀ የላለቀይ (ወልድ) ባራስ ጋር እሲቃን።
25) ሊልጦፍ ትሎን እመሽብኛን፥ ሊልሞት ትሎን እሶጅብኛን ባት ኡማርቴ።
#በሂልቅ ምስት ደር ያለይ መህማቾት ወድድኩሙይ

Sunday, February 3, 2019

አሁኑኑ ተገባራዊ የማደረገ ልምድን ማዳበር

#አሁኑኑ ተገባራዊ የማደረገ ልምድን ማዳበር

“እስከ ጨረቃ ውልደት ድረስ ይተኛል ቀን በፀሀይዋ ሙቀት ሲዝናና ይውላል፣ ኑሮውን በሙሉ "ነገ፡እሠራዋለሁ" ሲል ያሳልፈዋል፣ ምንም ነገር ሳይሠራም ይሞታል፡፡'
                                  ጀምስ ስስበሪ

ሁላችንም ብንሆን አንድን ነገር ላለመሥራት ስንፈልግ ሌላ ጊዜ አንሠራዋለን ብለን የማዘግየት ልማድ አለን፡፡ ቢያንስ እኔ አንዲህ ዓይነቱ ልምድ እንዳለኝና ብዙ ጊዜ በኋላ ላይ እንደምፀፀትበት አውቃለሁ። ነገሮችን ማዘግየት መጥፎ ወደሆኑ አስተሳሰቦች ይመራናል፡፡ ነገሮችን ማዝግየቱ ከመሥራቱ የባሰ ውስብስብ ስሜት ውስጥ ይክተናል፡፡

#የተጠናቀቀ ሥራ እርካታና ኃይልን የሚያጐናጽፍ ሲሆን ያልተጠናቀቀ ሥራ ግን ኃይልን ይመጥጣል! እርካታም ያሳጣል፡፡

#በጐ አመለካከትን ለማዳበር ፍላጐት ካለን ዕቅዶቻችንን መጠናቀቅ በሚገባቸው በተገቢው ጊዜ እያጠናቀቅን ሕይወትን ዛሬን ብቻ
አንደምንኖራት አድርገን አንኑራት፡

“ትልቅ ልጅ ስሆን ይህንንና ያንን አደርጋለሁ”. . . ብሎ በህፃንነቱ ዕቅድ ያወጣ አንድ ሰውዬ ነበር፡፥ ትልቅ ልጅ ሲሆን ደስተኝነት የሚሰማው የኮሌጅ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ እንደሆነ ተናገረ፡ የኮሌጅ ትምህርቱን አንዳጠናቀቀ ደግሞ የመጀመሪያውን ሥራ እስካላገኘ ድረስ ደስታ አንደማይሰማው ሲናገር ተደመጠ። ሥራ በያዘበት ቅፅበት ትዳር ካልያዘ
በቀር እንዴት ደስተኛ እንደሚሆን እንቆቅልሽ እንደሆነበት አወጋ። ትዳር አንደያዘ ደግሞ ልጆቹ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ከማየት የበለጠ ደስታ
እንደማይኖር መናገሩን ሰዎች ሰሙ፡። ልጆቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ደስታ የሚያገኘው ጡረታ በወጣበት ቀን እንደሚሆን ተነበየ፡፡
ጡረታ የወጣ ጌዜስ ምን ይታየው ይሆን?

አንዳንድ ሰዎች ነገሮችን የማዘግየት መጥፎ ልምዳቸውን ኃይለኛና ጥልቅ በሆኑ ቃላት ጀርባ ሸሸገው  ያዳብሩታል
ለምሳሌ "ጥናት እያደረኩበት ነው" በማለት ድክመታቸውን በውብ ቃል ይሸሽጉታል፡፡ እነኚህ
ሰዎች ያልተረዱት ነገር ቢኖር በጥናት ተቀፅላ የመሆን በሽታ እየተሰቃዩ እንደሆነ ነው፡፡

ሌላም "“አየተዘጋጀሁበት ነው!" የሚል ዓይነት አባባል ኣለላችሁ፡፡
ከአንድ ወር በኋላም እየተዘጋጀ ነው፡፡ ስድስት ወራት ካለፉ በኋላም ምላሹ
ያው "እየተዘጋጀሁ ነው” የሚል ነው፡ ታድያ እኚህ ሰዎች “ሰበብ የመፍጠር” በሽታ ሰለባ እንደሆኑ ሰው ካልነገራቸው በምን ማወቅ ይችላሉ?
ሕይወትኮ የምትገዙትን ልብስ አንደ መሞከር ዓይነት አይደለችም፡፡ ስለ ሕይወት የፈለጋችሁን ፍልስፍና ብትክከተሉም ከዚህ "ሕይወት" በተሰኘው ጨዋታ ውስጥ ያለን ዕድል አንድና በድጋሚ የማይገኝ ስለመሆኑ አትከራከሩም፡፡ ያንን ዕድል ማባከን የሚፈጥረው መዘዝ አከባድና አስከ ቀጣዩ
ትውልድም ሊጓዝ የሚችል ነው፡፡

አሁን ስንት ሰዓት ነው? የት ነው ያለነው? ለሚሉት ሁለት ጥያቄዎች ምላሾቹ አሁን እና አዚህ የሚሉት ቃላት ናቸው፡፥
ስለዚህ አሁኑኑ ያለንበትን ሁኔታ ምርጥና በጐ በማድረጉ ላይ እንትጋ በነገራችን ላይ ስለ ወደፊቱ ማሰብ የለብንም እያልኩኝ አይደለም፡፡ ግን የአሁኑን
ጊዜያችንን ምርጥ ካደረግነው ለቀጣዩ ሕይወታችን ምርጥ ዘር እየዘራን ነው ማለት ይቻላል፡፡

በጐ አመለካከትን የማዳበር ፅኑ ፍላጐት ካለን ነገሮችን በይደር የማዘግየት ልምዳችንን እርግፍ አድርገን በመተው "አሁኑኑ የመሥራት" ልምድ ማዳበር ይጠበቅብናል

#በሕይወት ውስጥ የመጨረሻዎቹ አሳዛኝ ንግግሮች፡-
"ቢሆን ኖሮ. . "
“ባላደርገው ኖሮ. . ."
“ላደርገው እችል ነበር. . "
"ባደርገው ጥሩ ነበር. . '"
“ትንሽ ጠንቀቅ የማለቱን ዕድል አግኝቼው ቢሆን ኖሮ. . ."

“ዛሬ ልትሰራው የምትችለወን በፍፁም ለነገ አታሳድረው"
                           ቤንጃሚን ፍራንክሊን

እርግጠኛ ነኝ ሁሉም አሸናፊዎች ነገሮችን ለነገ ማስተላለፍ ይገደዱ ነበር፡፡ ግን በፍጹም ለዚያ ስንፍና አልተንበረከኩም፡፡
ሰዎች "ከሚቀጥሉት ቀናቶች ውስጥ ባንዱ አደርገዋለሁ" ሲሉ ከሰማችሁ በፍፁም አንደማያደርጉት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ፡
አንዳንድ ሰዎች ገና ከቤት ሳይወጡ መንገዱ ላይ ያሉት መብራቶች በሙሉ አረንጓዴ እንዲሆኑላቸው ይፊልጋሉ፡፡ ያ ደግሞ የሚሆን አይደለምና
ገና ሳይጀምሩት ተሸናፊ ይሆናሉ፡፡ ተሸናፊነታቸው ገና ከመነሻው ላይ ነው፡

“ሌላ ጊዜ አደርገዋለሁ” ማለትን አቁሙ፤ ነገሮችን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍን የምናቆምበት ትክክለኛው ወቅት አሁን ነው።
           ለአሸናፊነት መገዛት ከሚለው    
          መፅሃፍ የተወሰደ

Tuesday, January 15, 2019

ሙስሊም ሳይንቲስቶች

#ቀደምት የሙስሊም ተመራማሪዎች እና ሳይንቲስቶች

#ጃቢር ኢብኑ ሀያን

ጃቢር ኢብኑ ሀያን የመካከለኛው ዘመን የኬሚስት ሊቁ ጀብር የሚባል
ሲሆን “የኬሚስትሪ አባት” በመባል በስፋት ይታወቃል።
ሙሉ ስሙ አቡ ሙሣ ጃቢር ኢብኑ ሀያን የሆነው ጃቢር አልፎ አልፎ
አል ሀራኒ እና አል ሱፊ በሚባሉ ስሞችም ይጠራል። ጃቢር አባቱ
የመድሃኒት ቀማሚ (አጣር) ናቸው። ትክክለኛ የተወለደበትን ቀን
ለማወቅ ተጨማሪ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም እንደ አጠቃላይ ግን
ጃቢር በ776 አካባቢ ኩፋ ውስጥ ነበር ህክምናን እና ኬሚስትሪን
ያዘወትር እንደነበር በታሪክ አጥኚዎች መካከል ስምምነት አለ።
ጃቢር በኢማም ጃዕፈር አስ ሣዲቅ እና የኦማያድ ሠርወ መንግስት
ልዑል በሆነው ኻሊድ ኢብኑ የዚድ ሥር ሆኖ ነው ትምህርቱን
የተከታተለው። ህክምናን የተማረው ገና በልጅነቱ በባርማኪ ወዚር
ቤት ሆኖ በአባሲድ አገዛዝ ኸሊፋ ሃሩን አር ረሺድ ዘመን ነበር።
ለባርማኪስ መውደቅ የተወሰነ ሚና የነበረው ሲሆን በወቅቱም ምድር
ቤት ውስጥ ታስሮ ነበር። ጃቢር የሞተው እ.ኤ.አ. በ803 ነው።
ማክስ ሜየርሃፍ (Max Mayerhaff) እንዳለውም
        
  በአውሮፓ የኬሚስትሪ እድገት በቀጥታ መመለሻው ጃቢር
                  ኢብኑ ሀያን ነው ብሏል።
ጃቢር በኬሚስትሪ ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው። ወደ ዘመናዊው
ኬሚስትሪ ለማደግ መሠረት የሆነውን ተግባር ተኮር
(experimental investigation) የኬሚስትሪ ምርምርን ለዓለም
ያሣወቀው እርሱ ነበር። እጅግ የታወቀው ላቦራቶሪው ፍርስራሹ
ለዘመናት የቆየ ቢሆንም ነገር ግን ጃቢር እውቅናን የተጎናፀፈው
በመቶ ትላልቅ ድርሰቶቹ ምክኒያት ነበር። ከነኚህም መካከል ሀያ
ሁለቱ ከኬሚስትሪ ጋር የተያያዙ ናቸው።
ለኬሚስትሪ መሠረት ከሆኑትና የሱ አስተዋፅኦ ከታከለባቸው ነገሮች
መካከል የኬሚስትሪን ሣይንሣዊ ዘዴዎች በላቀ መልኩ ማሣደግ
ሲሆን ማድረቅ (ክሪስታላይዜሽን)፣ ማጣራት (ዲስቲሌችን)፣
ማጠጠር (ካልሲኔሽን)፣ ማቅለጥ (ሰብሊሜሽን)፣ ማትነን
(ኢቫፖሬሽን)፣ እና የተለያዩ ለዚሁ ምርምር የሚያግዙ ቁሣቁሦችን
ያጠቃልላል። ያልጠሩ ሀሳቦች ተንሰራፍተው በሚገኙበት በዚያ ዘመን
ኬሚስትሪ እንደ አንድ የሣይንስ ዘርፍ ሆኖ በዐረቦች ዘንድ በእጅጉ
ተደራጅቶ ነበር። ኬሚስትሪ የሚለው ቃል የመጣውም “አል-ኪሚያ”
ከሚለው የዐረብኛ ቃል ነው። ይህም በሙስሊም ተመራማሪዎች
በሰፊው ጥናት ተደርጎበት ተሻሽሏል።
የጃቢር ተግባር ተኮር ምርምር ከፍተኛ ስኬት የነበሩት የተለያዩ
ማዕድናትን እና ሌሎችን አሲዶችን ማግኘቱ ላይ ነበር። እነኚህም
ለመጀመሪያ ጊዜ በርሱ አለምቢክ (አለንቢቅ/alembic) የማጣሪያ
መሣሪያ ውስጥ የተዘጋጁ ነበሩ። ለኬሚስትሪ መሠረታዊ ባህሪ
በርካታ አስተዋፅኦዎችን ከማድረጉም በላይ አዳዲስ ውህዶችን
(compounds) እና የኬሚካል አሠራር ዘዴዎችን እንዲሁም በርካታ
ተግባር ተኮር የሆኑ ኬሚካላዊ ሂደቶችን (applied chemical
processes) አጎልብቷል። በዚህም ሰፊ ሥራው የተነሣ በተግባር
ተኮር ሣይንስ ዘረፍ መሪና ሞዴል ተጠቃሽ ለመሆን ችሏል። በዚሁ
ዘርፍ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የተለያዩ ብረታ ብረቶች
ስለሚዘጋጁበት ሁኔታ፣ የሽቦ (steel) አሠራር፣ የልብስ አነካከር፣
የቆዳ አዘገጃጀት፣ ውሃ የማያስገቡ ልብሦችን ስለ መቀባት፣
በመስታወት ሥራ ማንጋኒዝ ዳይ ኦክሣይድን መጠቀም፣ ዝገትን
መከላከል፣ በወርቅ መሙላት፣ ቀለማትን መለየት፣ ቅባቶች እና
የመሣሰሉት ይጠቀሳሉ። በዚህ ረጅምና እልህ አስጨራሽ የተግባር
ምርምር ወቅት ወርቅን ለማሟሟት የሚያስችል አኳራጂያ ማግኘት
ችሏል። አለምቢክ የሱ ትልቅ ፈጠራ ሲሆን ይህም የማጣራትን ሥራ
ቀላልና ስልታዊ በሆነ መልኩ እንዲሆን አድርጎታል። ጃቢር ከዚህም
በላይ በተግባር ምርምሮችና በትክክለኛነታቸው (experimentation
and accuracy) ላይ ትልቅ ትኩረት የመስጠትን መሠረት ጥሏል።
ጃቢር ከባህሪያቸው በመነሣት ንጥረ ነገሮችን (substances)
በሦስት የተለያዩ አይነቶች ይከፍላቸዋል። የመጀመሪያው ሰፒሪት/
መንፈስ ማለትም በሚሞቁበት ጊዜ የሚተኑት ሲሆኑ እነኚህም
ካምፎር፣ አርሰኒክና አሞኒየም ክሎራይድን የመሣሰሉትን ይይዛል።
ሁለተኛው ብረት ነኬ ሲሆን ይህም ወርቅን፣ ብርን፣ መዳብን፣ ሊድ እና
ብረትን ያጠቃልላል። በሦስተኛው ምድብ ውስጥ ደግሞ ወደ
ዱቄትነት/ብናኝነት የሚለወጡ ነገሮችን አስቀምጧል። ይህም
ክፍፍል ኋላ ላይ ነገሮችን ብረት ነኬ (metals)፣ ብረት ነኬ ያልሆኑ
(non-metals) እና በቀላሉ የሚተኑ (volatile) ተብለው
ለተከፈሉበት ሁኔታ መሠረትን ጥሏል።
ጃቢር ምንም እንኳ በኬሚስትነቱ ቢታወቅም እንደ አልኬሚያ ባለሙያ
ግን ምናባዊ የተከበሩ ማእድናት አዘጋጃጀት ለይ ትኩረት አድርጎ
የተንቀሣቀሠ አይመስልም። ባይሆን ትልቁን ጉልበቱንና ጊዜውን
የጨረሠው መሠረታዊ የሆኑ ኬሚካለዊ አሠራሮች አንዴት
እንደሚያድጉና በኬሚካል ፅግበራ (chemical reactions) ዙሪያ
ነበር። በዚህም የኬሚስትሪ ሣይንስ ከአልኬሚ ምናባዊ እንቆቅልሽ
ጎልብቶ ይወጣ ዘንድ ረድቷል። በኬሚካላዊ ፅግበራ በርካታ የተለያዩ
ውጤቶች ሊገኙ እንደሚችሉ አፅንኦት ሠጥቷል። በዚህም የተነሣ
የኮንስታንት ፕሮፖርሽን ህግ (the law of constant
proportions) የማግኘቱ መንገድ ቀላል ሊሆን ችሏል።
በጃቢር የፅሁፍ ክምችት ውስጥ በርካታ የመፅሃፍ ቅጂዎች
ተካተዋል። ከኬሚስትሪ በተጨማሪ ለህክምና እና ለሥነ ከዋክብት
ጥናትም የጃቢር አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። በኬሚስትሪ ዙሪያ
ከሚጠቀሱ መፅሃፎች መካከል “ኪታብ አል-ኪሚያ” እና “ኪታብ
አስ-ሰቢኢን” ይጠቀሳሉ። መፅሃፎቹም ወደ ላቲን እና በርካታ
የአውሮፓ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል። እነኚህም ትርጉሞች በአውሮፓ
ውስጥ ለክፍለ ዘመናት ገነው የቆዩ ሲሆን ዘመናዊዉ ኬሚስትሪ
መከሠትም አቢይ ምክኒያት ነበሩ። ጃቢር ይጠቀምባቸው የነበሩና
የዛሬው የአውሮፓውያኑ ቋንቋዎች የሚጠቀሙባቸው አልካሊ
(alkali) እና የመሣሠሉት በርካታ ከምርምሩ ጋር የተያያዙ ቃላት
የሳይንስ መዝገበ ቃላት ክፍል ሊሆኑ ችለዋል። ከመፅሃፎቹ ታርመው
ለህትመት የበቁት የተወሰኑት ብቻ ሲሆኑ በርከት ያሉትና በዐረቢኛ
ቋንቋ የተፃፉት ግን ዛሬም ድረስ ትኩረት ተነፍጎአቸው ሣይታተሙ
ተቀምጠዋል።
በሱ የፅሁፍ ክምችት ውስጥ ሁሉም የሱ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ
ስለመካተታቸው ጥያቄ ያለ ሲሆን ክምችቶቹም የሱ ስብስቦች ብቻ
ናቸው ወይንስ ኋላ ላይ የመጡ ተከታዮቹ ትንታኔ ተካቶባቸዋል የሚል
ጥያቄም አለ። እንደ ሣርቶን (Sarton) አባባል ከሆነ የሱ ሥራዎች
ስለመሆናቸው ልናረጋግጥ የምንችለው ሁሉም መፅሃፎቹ የታረሙና
የታተሙ እንደሆነ ብቻ ነው። በፅሁፉ ውስጥ የተካተተው ሃይማኖታዊ
አመለካከቱና የፍልስፍና ጭብጡ ምንም እንኳ ትችት የገጠመው
ቢሆንም ስለ ትክክለኛታቸው የሚነሣው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ሊካድ
የማይችል ሀቅ ቢኖር ጃቢር በዋናነት ለሃይማኖቱ ሳይሆን
ለኬሚስትሪ ሣይንስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ መሆኑን ነው።
በርካታ ግኝቶቹ ለምሣሌ አሲድ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘቱ በተለይ
ናይትሪክ፣ ሃይድሮ ክሎሪክ፣ ሲትሪክ፣ እና ታርታሪክ አሲድ እና ስልታዊ
ሙከራዎቹ እጅግ የተዋጣላቸው ነበሩ። ይህም በመሆኑ ነው ይህ
ሰው የዘመናዊው ኬሚስትሪ አባት (father of modern
chemistry) ተብሎ ሊታይ የቻለው። ማክስ ሜየርሃፍ (Max
Mayerhaff) እንዳለውም በአውሮፓ የኬሚስትሪ እድገት በቀጥታ
መመለሻው ጃቢር ኢብኑ ሀያን ነው ብሏል።

በሌላ ጊዜ የሌሎች ሙስሊም ተመራማሪዎችና ሳይንቲስቶች
አስተዋውቃቹኋለው ቸር ሰንብቱ አላህ ሰላማችሁን ያብዛላችሁ

Monday, January 14, 2019

.
“አስራ አንዱ የአጼ ሐይለሥላሴ ፀረ ሙስሊም እስትራቴጂዎች”
አፄ ኃይለ ሥላሴ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱ የኢትዮጵያ አፄዎች
አንዱ እና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ዘመን አይሽሬ ግፍ ከፈጸሙ
ንጉሦች አንዱ ነው። አምደኛችን አህመዲን ጀበል አገራዊና
ሚስጥራዊ ሠነዶችን አገላብጦ የንጉሡን 11 ፀረ-ሙስሊም
እስትራቴጂዎች ነቅሶ አውጥቷል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ኢስላማዊና ክርስቲያናዊ መንግሥታትን
አስተናግዳለች። ሕዝበ ሙስሊሙ ለሺህ ዓመታት ገደማ በተለያዩ
የሀገሪቱ ግዛቶች ውስጥ የራሱ የሆኑ መንግሥታት ነበሩት።
እስልምናን ለማዳከም፣ብሎም ከመላው ሀገሪቱ ለማጥፋት ሆን
ብለው በተሸረቡ ሴራዎች ተከተታይ ዘመቻዎችም ተደርገዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ዕውን ሆነው የነበሩ ኢስላማዊ
ሥልጣኔዎችም በተደጋጋሚ በተካሄዱ ዘመቻዎች ተደምስሰዋል።
ለረጅም ዘመናት የነበሩት ኢስላማዊ መንግሥታት ስለመኖራቸው ሁሉ
እንዲዘነጋ ተደረገ።አብዛኛዎቹ የት አካባቢ እንደነበሩ እንኳ በጥናት
እንጂ በቅርሳቸው እንዳይታወቁ ተደርገው ጠፉ። በተለይ
ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኋላ በአውሮፓውያኑ እገዛና
ሞግዚትነት የክርስቲያኑ መንግሥት የሙስሊሞችን ኃይልና ሕልውና
ደፍጥጦ አገሪቷን ‹‹የክርስቲያን ደሴት›› በሚል ፈሊጥ ሙሉ በሙሉ
በቁጥጥሩ ሥር አደረጋት።
ኢስላምን የማዳከሙ ዘመቻ እየተጠናከረና እየተባባሰ ሄደ።
ሙስሊሙ ለዘመናት ይደርስበት የነበረው የሃይማኖት ጥቃት
ቀጠለ።በወረራ የተቋቋመው ማዕከላዊ መንግሥትም ለኢስላምና
ለሙስሊሙ የሚሰጠው ስንዝር ሥፍራ አልነበረውም።
እንደዛሬው ሁሉንም በእኩል ዓይን የሚያይ ዴሞክራሲያዊ ሕገ
መንግሥት (ይህ ጽሁፍ ሲወጣ ኢህአዴግ በሙስሊሙ ላይ የጥፋት
ሰይፍ
በግልጽ አልመዘዘም ነበር) ባልነበረበት በዚያ ዘመን ሙስሊሙ
የሀገሪቷ ጠላት ተደርጎ ተፈረጀ።
ኢስላማዊ ማንነቱ በኃይል የተጨፈለቀበት ሙስሊም ላዩን ሲታይ እጅ
የሰጠ ቢመስልም
በውስጡ ግን የአፄዎቹ ተቃዋሚ ሆኖ ቀጠለ።
አፄዎቹ በግልጽም ሆነ በስውር ሙስሊሙን ለማዳከም በርካታ
ተግባራትን ፈጽመዋል።
ምናልባትም ከጎንደሩ አፄ ፋሲለደስ በስተቀር ሁሉም አፄዎች ከዚህ
ተግባራቸው የራቁ አልነበሩም።
በአሁን ሰዓት ያሉ የነርሱ ርዝራዦች የአፄው ሥርዓት አራማጅ የነበሩ
ግለሰቦችን የሀገር ባለውለታና ጀግና አድርገን እንድንቀበላቸው ብዙ
ቢጣጣሩም በሙስሊሙ ላይ ያደረሱትን
ስቃይና መከራ በየአጋጣሚው ከማውሳትም ሆነ ከመጻፍ ሙስሊሙ
ቸል ሊል አይገባውም።
Click ☞ bit.ly/1PBnJ4l
click☞ bit.ly/1QeueX3
ምክንያቱም እነዚህን ግለሰቦች እንደ ጀግና መቀበል በራሱ የጭቆና
በትራቸውን ባሳረፉበት
ተጨቋኝ ሕዝብ ላይ ማሾፍ፣ባለፈ ጠባሳው መደሰት፣ወደፊትም
ተመሳሳይ ነገር ሊፈጠር የሚችልበትን እድል ሙሉ በሙሉ
አለመዝጋት፣ መስፈን የሚገባውን የይቅርታ መንፈስና
የዴሞክራሲያችንን ዘላቂነት አደጋ ላይ መጣል ነው።
የአፄ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት ፀረ-ኢስላም ስትራቴጂዎች በጣም
በጥቂቱ ቀንጨብ በማድረግ አስነብባችኋለሁ።
ኃይለ ሥላሴ ፀረ- ሙስሊም ዘመቻውን ማጧጣፍ የጀመረው
ገና ሥልጣን ሳይቆናጠጥ ነበር። ወንበር አያያዙ ራሱ ሙስሊሙ
ላይ በተሸረበ ሴራ ነበር።
‹‹እስላም አይነግስም!›› በሚል በመኳንንትና በቀሳውስት የጋራ
ፀረ–ኢስላም አድማ ነበር
ግንባር ፈጥረው ልጅ እያሱን የጣሉት። እንዲህ ሲሉ ነበር
ያወጁት፡- ‹‹አዋጅ! የኢትዮጵያ
ሕዝብ ስማ! መስሚያ አይንሳህና ልጅ እያሱ ወደ እስላም
ሃይማኖት ስለገቡ መንግሥት አይገባቸውም… ከአዋጁ በላይ
የእስላም ወገን ሆኖ ሲረዳ የተገኘ አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል››
አፄ ኃይለ ሥላሴ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በሕገ መንግስቱ ላይ
በግልፅ ሥልጣን የሚገባው ለክርስቲያኑ ብቻ እንደሆነ ደንግጓል።
ለይስሙላ ያህል ራሱን ለሁሉም ኢትዮጵያውያንተቆርቋሪ መሪ
ለማስመሰል አስቂኝ ሙከራዎችን አድርጓል። ነገር ግን የዚህ
ጽሁፍ ዓላማ በኢትዮጵያ ኢስላምንና ሙስሊሙን ለማዳከም
የፈፀማቸውን (ያስፈፀመውን) ስውር ሴራዎች በጥቅቱ ማሳየት
ስለሆነ ለጊዜው እዚያ ውስጥ አልገባም።
የኃይለ ሥላሴ መንግሥት ፀረ-ሙስሊም ስትራቴጂዎች በርካታ
ቢሆኑም ለዛሬ አሥራ አንዱን ብቻ ለማሳየት እጥራለሁ።
መልካም ንባብ።
①. ☞ሙስሊሙን ማክፈር (ክርስትና ማስነሳት)
ይህን ዓላማ ከዳር ለማድረስ በወቅቱ ‹‹የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገስት
የሕዝብ ኑሮ እድገት ሚኒስቴር›› የሚል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት
በማቋቋም ሙስሊሙን ኦርቶዶክስ ክስቲያን ለማድረግ ተጥሯል።
በተጨማሪም የብሔር ብሔረሰቦችን
ቋንቋ በመጨፍለቅ አማርኛን ብቻ ለማጠናከርም ተሞክሮ ነበር ።
የዚህን መሥሪያ ቤት ገመና ወደፊት የምናየው ይሆናል።
ሙስሊሙ በአንጡራ ኃብቱ ጭምር
የሚከፍለው ግብር ክርስትናን ለማጠናከር ሲውል ነበር።
ለአብነት ያህል የወሎው ጳጳስ በመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ
በመንግሥት ባጀት ሙስሊም ህጻናትን በጥቅም በማታለል
አጥምቀዋል።
☞ በግንቦት 15/1944 በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወሎ ሙስሊሞች
ለመንግሥት አቤቱታ አቅርበዋል። በደብዳቤያቸው ላይም ‹‹በወሎ
ግዛት የተሾሙት ጳጳስ ልብስና ጉርስ እየሰጡ የእስላሞችን ሴቶችና
ልጆች እየሰበኩ ክርስቲያን ለማድረግ ስለሚሞክሩ፣ ይህ ሥራ
ከሁለቱ ሃይማኖት ወጥተው ሌላ መንፈስ የሚሰማውን ሕዝብ
ስለሚፈጥር፣ የነዋሪዎችን ሕሊና ስለሚያናውጥ ለስብከት
የሚያወጡት ገንዘብ ለትምህርት ታክስ ከወጣው ተቀንሶ የተሰጣቸው
ነውና…›› ሲሉ ገልጸው ነበር።
በዚሁ ጉዳይ ላይ የደሴ ሙስሊሞች በበኩላቸው በሚያዚያ 5 ቀን
1944 ዓ.ል እንዲህ ሲሉ
ለመንግሥት አቤቱታ አቅርበዋል፡-
‹‹……የልጆች አባት የሆንን ሁሉ በጣም ከፍ ባለ ደስታ የሞላን
ሆነን የትምህርታቸውን ፍሬ
እናገኛለን በማለት ስንተማመን አሁን በወሎ ጠቅላይ ግዛት
የተላኩት ቄስ ብፁዕ አባት የሆኑት ሕዝቡን በትምህርት
በማሰልጠን ፋንታ ከላይ የተጠቀሰውን ‹ሃይማኖት የግል አገር
የጋራ›
የሚለውን በመዘንጋት ጥቂት ገንዘብና ቁምጣ፣ሱፍ፣ ኮት
እየሰጡ ብዙ እስላሞች ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት
እንዲጠመቁ ስላደረጉ ሃይማኖት የግል አገር የጋራ በሚለው
የፍቅር ሰንሰለት ተሳስረን የምንኖረውን ወንድማማቾች
የሚለያይ መስሎ ስለታየን ለክብርነትዎ ማመልከት ግዴታ
ሆነብን።››
Click ☞ bit.ly/1PBnJ4l
②. ☞ሙስሊሙን ነጋዴ ማክሰርና በኢኮኖሚ ማዳከም: –
ሙስሊሙ የሃይማኖቱን ነፃነትና መብቱን ለማስከበር ሲያደርግ
በነበረው ትግል ውስጥ ለሃይማኖታቸው ሲሉ ካላቸው ሃብትና ንብረት
ላይ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ጉዳይ ወጪ ሲያደርጉ
የነበሩትን ሃብታም ነጋዴዎች በዘዴ ማክሰር፣ ከመጠን በላይ ግብር
መጫን እና በሰበብ አስባቡ ንብረት መውረስ ወዘተ…. የአፄ ኃይለ
ሥላሴ መንግሥት የተከተለው ስትራቴጂ ነበር።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጭቆና በቃን በማለት በ1956 ዓ.ል
በሚስጥር በመገናኘት አንድ ማኅበር አቋቁመው ነበር።
በአፄው የደህንነት መሥሪያ ቤት በ10/10/1957 በተፃፈ
ሚስጥራዊ ሰነድ ላይ ሙስሊሞች ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ
በዝርዝር ገልጾ ለውሳኔ ለንጉሱ አቅርቧል።
ለምሳሌ:-
በሰነዱ ላይ ድርጅቱን በገንዘብ በመደጎም ገንዘብ ያዥ የነበሩት አቶ
ዑመር ኢማም ላይ እንዲወሰድ የታቀደው እርምጃ ለዚህ ጥሩ ማሳያ
ይሆናል።
‹‹አቶ ዑመር ኢማም የማኅበሩ ግምጃ ቤት፡- ይህ ሰው ነጋዴ
በመሆኑ በንግዱ ላይ የገንዘብ ጉድለት እንዲፈጠር በዘዴ
ቢደረግ የኑሮ ትግሉ ወደ ተንኮል ላይገፋፋው ይችላል። የንጉሱን
አገዛዝ የሚነቅፍን ከአሁኑኑ ካላስወገድን ለወደፊቱ ዓላማ
ለማቅናት ያስቸግራል›› ሲል ያትታል።
ይህ አይነቱ ሙስሊም ነጋዴን በዘዴ የመጣል ስትራቴጂ በስንቱ ላይ
ተተግብሮ እንደሆን አላህ ይወቀው።
በሰለጠነው አለም የትናንት ታሪክን ማውጋት በዛሬው ተጨባጭ
የሚፈጥረው ምንም አይነት አሉታዊ ቅራኔ ስለሌለው ነጻ የመሆን
ስሜት ይሰማል::
☞በሁለተኛው አለም ጦርነት በሚሊዮኖች
የተጨፋጨፉት አውሮፓውያን ዛሬ በአንድ ለመጣመር ደፋ ቀና
የማለታቸው ምስጢሩ ትናንትናን ይቅር በማለታቸው ነው::
ወደሀገራችን እውነታ ስንመለስ ይሄ ቀና እይታ የተምታታባቸው ሰዎች
ይስተዋላሉ:: በብሄር ወይም ሀይማኖት ላይ የተሰሩትን ወንጀሎች
እነሱ ሳይከሰሱበት ደርሰው ተቆርቋሪ ለመሆን ይሞክራሉ::
በተለያዩ ነገስታት በኢትዮጵያዊው ሙስሊም
የተፈጸመው ግፍ መነገሩ ህዝበ ክርስቲያኑ ወይም ቤተክርስትያን
እንደመኮነን የሚቆጥሩት የዋሆች ይስተዋላሉ::
የትናንቱ ታሪካችን መማማሪያ እንጂ በሀሳብ መወጋገሪያ መሆን
የለበትም::አንዳችን ሌላችን ከልብ በመደማመጥ ለልጆቻችን
የተሻለች ኢትዮጵያን መቅረጽ ያስፈልገናል::
አጼ ሀይለስላሴ በተፈጥሮው ንቁ፣ፈጣን፣ እንደይሁዳ እጅግ በጣም
ተጠራጣሪ፣ ጨካኝ፣ለስልጣንና ክብሩ ማንኛውንም መስዋእት
የሚከፍል ገዥ ነበር::
በአድዋ ጦርነት መሪ የነበረው ወላጅ አባቱ ራስ መኮንን በምንሊክ
ዘንድ የነበረውን ከበሬታ ተጠቅሞ በአስራ ሶስት አመት እድሜው
ደጃዝማች መሰኘት ቻለ::
በተከታዩ አመት በ1898 አባቱ ራስ መኮንን ቁልቢ ውስጥ ሞተ::በአጼ
ምኒሊክ ጦር ከሙስሊሞች የተነጠቀችው ሀረር የመስጂዶቿ ሚናራ
እየተነቀሉ
መስቀል የሚተከልበት አሳዛኝ ወቅት ላይ ደጃዝማች ተፈሪ (አጼ
ሀይለስላሴ ) በወንድምነት የማይዘክረው የሀረር ገዥ ወንድሙ
ይልማ ራስ መኮንን ሞተ ተባለ::የይልማን ሞት ከደጃዝማች ተፈሪ
(ከአጼ ሀይለስላሴ) የሚያያዙ አሉ::
ደጃዝማች ተፈሪ ወንድሙ ይልማን ካስወገደ ወዲያ የሀረር ሀገረ ገዥ
የነበሩት ባልቻ አባ ሳፎ (አባ ነፍሶ) በዘዴና ጉልበት ገለል አድርጎ
ስልጣኑን ተቆናጠጠ::
click☞ bit.ly/1QeueX3
“የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት በቅጽ 01 ቁጥር 06 የጥቅምት ወር
2003 እትሟ የመጽሄቷ አምደኛ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፅሁፉን
ይቀጥላል…..
③. ☞ሙስሊሙን ከአካባቢው ማራቅ
የሙስሊሙን መብት ለማስከበር ትግል ሲያደርጉ የነበሩ
ሙስሊሞችን ከአካባቢው ማራቅን (ማስወገድን)አፄው እንደ
ስትራቴጂ ሲጠቀምበት ነበር።
በተለይ የመንግሥት ሠራተኛ ከሆነ ከነበረበት አካባቢ ራቅ ወዳለ
ሥፍራ በዝውውር (ምደባ)፣ እድገት ወዘተ ሥምና ሽፋን ማስወገድን
ይጠቀም ነበር።
ለምሳሌ:-
ከላይ በጠቀስነውና ‹‹የበጎ ሥራ መረዳጃ ማኅበር›› በሚል
የሙስሊም ድርጅት መሪ በነበሩት አቶ አብዱልከሪም በተባሉት
ሙስሊም ላይ ሊወሰድ የታቀደውን እርምጃ ማየት
እንችላለን። የደህንነት ሪፖርቱ፡-
‹‹አቶ አብዱልከሪም የተባለው ሰው የዚሁ ማኅበር ፕሬዝዳንት
የሆነው በማስታወቂያ ሜኒስቴር
ውስጥ የዶክመንት ክፍል ሠራተኛ…….በሹመት መልክ ራቅ
ወዳለ ጠቅላይ ግዛት እንዲዛወር ››5 ሲል ይገልጻል።
እንደዚሁም
☞የማኅበሩ ም/ሊቀመንበር በአቶ አሊ ሙሐመድ አብዱሰላም
ላይም የማራቅ እርምጃ እንዲወሰድ ቀርቦ ነበር።
ምስጠራዊው ዶክመንት እንዲህ ይላል፡-
☞‹‹አቶ አሊ ሙሐመድ አብዱሰላም ም/ፕሬዝዳንት፡- ይህ ሰው
አሁን የሚሰራው በፍርድ ሚኒስቴር በጠበቆችና ስታቲስቲክስ
ክፍል ስለሆነ ክርስቲያን በሚበዛበት አገር እንደ ጎጃም አይነት
ቦታ በመዛወር መልክ ቢሄድ ተባባሪ ሊያገኝ አይችልም።››
④.☞ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከፖለቲካ ማግለል
ሙስሊሞች በሀገራቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዳይሆኑ
በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ነበር።
ይህንንም ስትራቴጂ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥትም
ተጠቅሞበታል።
Click ☞ bit.ly/1PBnJ4l
click☞ bit.ly/1QeueX3
ከላይ በጠቀስነው ምስጢራዊ ዶክመንት ላይ ሙስሊሙን ከፓርላማ
ምርጫ ማሰናከል እንደሚገባ ተጠቅሷል። እንዲህ ይላል፡-☞ ‹‹አቶ
ሙሐመድ ኢብራሂም ሳብሬ የተባለው ዋና ጸሐፊ ነው
(የድርጅቱ)። ይህ ሰው አሁን ለፓርነት ምርጫ ገብቷል። ከዚህም
ምርጫ በምሥጢር እንዲሰናከል በማድረግ ኑሮው መጠነኛ
በመሆኑ የሞራል ውድቀት አግኝቶት ከተንኮሉ ሊወገድ
ይችላል።››
⑤. ☞ሙስሊሙን ከትምህርት ማደናቀፍ
ሙስሊሙ ከተማረ ራሱን፣ ሃገሩን፣ መብቱንና እምነቱን በሚገባ
ጠንቅቆ ያውቃል። መብቱን ይጠይቃል። ለመብቱና ለነፃነቱ
ይታገላል። በመንግሥት መዋቅርና ፖለቲካ ውስጥ ይሳተፋል።
ጭቆናን ለማስወገድ ስልት ይቀይሳል። የሃይማኖቱ ነጻነት
በተግባር እንዲተረጎም ይጣጣራል። የሚሸረብበትን ሴራ
ይበጣጥሳል። ይህ እንዳይሆን በማለም የአፄው መንግሥት
ሙስሊሙን ከትምህርት የማራቅን ስትራቴጂ ተከትሏል። ከዚህ
አልፎ ሊማር የሚሻ ሙ ስሊም እንኳ ካለ ከእምነቱ አልያም
ከትምህርቱ እንዲመርጥ ሲገደድ ነበር። አልያም ስለ ኢስላም
የማያውቅ (የማይቆረቆር) ዝንጉ ሙስሊም እንዲሆን ተጥሯል።
ሙስሊሙ ወላጅ በትምህርት ቤት ውስጥ የክርስትና ሃይማኖት
ትምህርት ይሰጥ ስለነበር ‹‹ልጆቼ ይከፍሩብኛል›› ሲል ልጆቹን
ከትምህርት
አራቀ። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚያዚያ 1 ቀን 1966 ዓ.ል
ለመንግሥት ካቀረቡት አንኳር ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ይህ
የትምህርት አድሎ ይቁምልን›› የሚል ነበር። እንዲህም ብለው
ነበር፡-
‹‹በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የሃይማኖትና የሞራል
ትምህርት የአንዱን ክፍል ሃይማኖት (ብቻ) የተከተለ እንደ
መሆኑ እስላሞች ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ
በመፍራት ወደ
ት/ቤቶች ሳይልኳቸው በመቅረቱ በዘመናዊ ትምህርት ያለንን
ተካፋይነት አዳክሞታል።››
የኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተጠና ዘዴ ነበር ሙስሊሙን ከትምህርት
ሲያርቅ የነበረው።
ጋዜጠኛ የነበሩት ሐጂ በሽር ዳውድ (አላህ ይማራቸውና) በአፄው
ዘመን ወደ አፋር ያቀናሉ።
በመንገድ ላይ ሳሉ እንደ ሁልጊዜው ሙስሊሞቹ አፋሮችና ኢሳ
ጎሳዎች እርስ በእርስ ይዋጉ ነበር። ‹‹ለምን መንግሥት
ውጊያውን አያስቆምም?›› የሚል ጥያቄ ውስጣቸው
ይፈጠርባቸዋል።
እንዲህ ይተርኩልናል፡- ‹‹‹ጋዜጠኛ ነኝ› በማለት ወደ
አውራጃው አስተዳደር ኮሎኔል ጽ/ቤት ብቅ አልኩ። እስላም
መሆኔን አላወቀም። አክብረው ተቀበሉኝ።
ቡና መጣና ፉት እያልኩ ከሁለቱም ጎሳዎች ነፍሰ ገዳዩ
እየተለቀመ ህጋዊ ፍርድ እየተሰጠ ከድሬዳዋ ጀምሮ እስከ
ናዝሬት ከተማ ባለው የዛፍ ግንድ ላይ አንድ መቶ ያህሉ ቢሰቀሉ
ሰላምና ፀጥታ ይሰፍናል። ሕዝቡም ሠልጥኖ ወደ ልማት ሥራ
ይዞራል።
ለምን ይህ አይደረግም?›› ስል ጠየቅኩ።
☞እርሳቸው ግን በጣም ደነገጡ። ፊታቸውን ኩምትር
ጭምድድ አደረጉና ሌባ ጣታቸውን ቀስረው አፍንጫቸውና
አፋቸው ላይ አድርገው ‹ኡስ ኡስ! ከኔ ሌላ ሰው አደራ
እንዳይሰማህ› አሉኝ።
ደንገጥ ብዬ ‹ምነው?› አልኳቸው።
እሳቸውም ‹ከቀይ ባህር ጀምሮ በወሎና በመንዝ ተራራ ስር
አልፎ እስከ ኬኒያ ባለው በዳና ሜዳ ላይ የሰፈረው ሕዝብ
እስላም መሆኑን አታውቅም? እነዚህ ጎሳዎች ተምረው
ቢሰለጥኑና አንድ
ቢሆኑ በአካባቢያቸው ካሉት ዐረብና እስላም አገሮች ጋር
እየተገናኙ ኢትዮጵያዊ ለሆነው የክርስቲያን ሕዝብ ከባድ የሆነ
ችግር
ይፈጥራሉና እንዲሁ ዘላን ሆነው እየተጋደሉ ይቆዩ የማለት
ጥናት ተደርጎ ከነገስታቶች የተሰጠ የበላይ መመሪያ መሆኑን
ጋዜጠኛ ሆነህ እንዴት አታውቅም?› አሉ።
ደንግጬ ከቢሯቸው ወጣሁ››
በትናንት ስህተት አግባብ ያለው እርምት መወሰዱ ለዛሬና ነገ መድህን
ነው:: የዛሬ ድርጊት የነገ ታሪክ ነውና እርምቱ ቅጣትም ሆነ ወቀሳ
በቀልን ባላዘለ መልኩ መስተናገድ ይገባዋል::
መንግስታት ለሰሩት መልካም በታሪክ ሲወደሱ እንደመኖራቸው
ለስህተታቸው መወቀስ፣መወገዝና መከሰሳቸው አግባብነት
አለው::ወደድንም ጠላን ትናንት እንደሰንሰለት ከዛሬ ጋር ጥምረት
አለው::ትናንት በብሄር፣በሀይማኖት ተበድለናል የሚሉ ወገኖች ሌላው
ቢቀር መደመጥ መቻል አለባቸው::የትናንቱ በደላቸውን በወጉ
ለማድመጥ ፈቃደኛ ሆኖ መገኘት ዛሬ ይቅር እንዲሉ
ይረዳቸዋል::ካሳ ባልጠየቁበት ወይም በማይጠይቁበት ሁኔታ
በደላቸውን መግለጻቸው መቃወም ግን እንዲያቄሙ ከመግፋት
የዘለለ ፋይዳ የለውም::
ኢትዮጵያዊው ሙስሊም በመሪር ጭካኔ ያጎሳቆሉት በዳይ ገዥዎች
መውቀሱ ዛሬ ለዚያ በደል በተጠያቂነት ማንም ላይ ጣት
መቀሰሩአይደለም:: ከዚሁ መሰረተ ሀሳብ ሳንወጣ ወደ ወጋችን
እንግባ::
ግራዝማች ተፈሪ መኮንን (አጼ ሃይለስላሴ) ከሲዳሞ ገዥነቱ
በመነሳት አዲስ አበባ ቤተመንግስት እስኪዘልቅ ደረጃ በደረጃ
የተጠቀመበት አንዱን በሌላው የመምታት ዘዴ የተሳካ ነበር::
ለዚህ እንደማሳያ ጥቂት ምሳሌ እንውሰድ ::አጼ ምኒሊክ አልጋ ቁራኛ
እንደሆነ የቤተመንግስቱን ስልጣን በሙሉ እጇ ላይ ያስገባቸው እቴጌ
ጣይቱን በልጅ ኢያሱ መትቷታል::
ከምኒሊክ ሞት በኋላ ጣይቱ ከአዲስ አበባ ቤተመንግስት
ወደእንጦጦ እንድትዘዋወር
ልጅ ኢያሱ የወሰኑት በሃይለስላሴ ታክቲክ ነበር::
የእህታቸው ወይዘሮ ስህን ልጅ መነን አስፋውን ለሃይለስላሴ የዳሩት
ልጅ ኢያሱም ከተንኮሉ ማምለጥ አልቻሉም:: እነ ፊታውራሪ
ሀብተጊዮርጊስ ዴነገዴና የአብያተ ክርስቲያናት ሰዎች ተጠቅሞ
ልጅ ኢያሱ ሰልሟል በማስባል አስፈንቅሏቸዋል::
ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወርም ሃይለስላሴ ወደ እንግሊዝ
ከመፈርጠጡ በፊት ጣሊያን ታነግሳቸዋለች በሚል ፍርሀት ልጅ
ኢያሱን
አስገድሏቸዋል::
አጼ ሃይለስላሴ በአልጋወራሽነቱ በንግስት ዘውዲቱ ዙፋን እንዳሻው
ማዘዙ የተቆጣው የንግስቲቱ ባል ራስ ጉግሳ ወሌን በጦርነት
ካስገደለው ሁለት ቀን በኋላ ንግስት ዘውዲቱም ሞተች ተባለ::
ንግስቷ በመርዝ እንደተገደለች ብዙም ሳያነጋግር ራስ ተፈሪ መኮንን
ጥቅምት23/1923 “ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሞአ አንበሳ
ዘእምነገድ የሁዳ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ፣ ”
በሚል መጠሪያ ዘውድ ደፋ::
ለስልጣኔ አይመቹኝም ብሎ የሚያስባቸውን በየተራ እየጠራረገ
አልጋውን ሲያደላድል ዙፋን ላይ በተቀመጠ አምስተኛ አመት ኢጣሊያ
ሀገራችን ወረረች::እሱም ቤተሰቦቹን ሰብስቦ ወደእንግሊዝ ኮበለለ::
⑥. ☞ሙስሊሙ በወሳኝ አገራዊ ጉዳይ እንዳይሳተፍ ማድረግ
የአፄው መንግሥት ሙስሊሙ በአገሪቷ ወሳኝ መዋቅር ውስጥ
እንዳይሳተፍ ሲታገል ነበር። የሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት፣ ሚኒስቴር
መሥሪያ
ቤት፣ ፖሊስ፣ ደህንነትና መሠል ወሳኝ የመንግሥት አካላት
ለሙስሊሙ ዝግ ነበሩ።
ለአብነት የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በ1948 በሚስጥር ያዘጋጀው
ሰነድ እንዲህ ይላል፡
– ‹‹የፖሊስ ጠቅላይ ሠራዊት ጽ/ቤት በዋናው መናገሻ ከተማ
በየጠቅላይ ግዛቱ አንዳንድ
የፖሊስ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያቋቋመው ስለላ የፀጥታ
ዘበኞች ማሠልጠን ጉዳይ በዚያ
በኩል ሊፈፀም ይችላል። ነገር ግን ለዚህ ጉዳይ የሚቀጠሩት
የፀጥታ ዘበኞች ክርስቲያን፣
አማርኛ የማንበብና የመፃፍ ችሎታ ያላቸውና አማሮች እንዲሆኑ
ስለሚያስፈልግ ጥንቃቄ
እንዲደረግበት ያስፈልጋል።››
click☞ bit.ly/1QeueX3
ይህም ብቻ ሳይሆን በኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግሥት ላይ ግልጽ በሆነ
ቋንቋ ሙስሊም የሀገሪቷ መሪ ሊሆን እንዳማይገባ ተጠቅሷል።
☞ኢትዮጵያ ሙስሊም ፕሬዝዳንት እንዳይኖራት ተደረገ።
☞የ1948 የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አዋጅ፣አንቀጽ 126 እንዲህ
ይላል፡-‹ ‹በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ማርቆስ
ትምህርት መሠረት የተቋቋመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን
የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት መሠረታዊ ቤተክርስቲያን ናት።
የንጉሠ ነገሥቱ ሃይማኖት ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ሃይማኖት መሆን
አለበት።መንፈሳዊ አገልግሎትም በሚደረግበት ሁሉ የንጉሠ
ነገሥቱ ስም ይጠራ።››
⑦.☞ ሙስሊሙ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳይወጣ ማገድ
ሙስሊሙ በትውልድ አገሩ የመኖሩ ምንነትና የሀገር ትርጉም አልገባ
ብሎት በምሬት እግሩ ወደ መራው አጎራባች አገር በብዛት ሲሰደድ
ነበር።
በሙስሊሙ ላይ የሚፀመው በደል ለዓለም ይፋ
እንዳይሆን የተወሰደው አማራጭ ደግሞ ከሀገር እንዳይወጡ ማገድ
ነበር።
ለምሳሌ☞ በ1942 ዓ.ል የተፃፈ ደብዳቤ ይህንን
ያስረዳል ‹‹ያለ ፍቃድ ወደውጭ አገር ይሄዳሉ ስለተባሉ
እስላሞችና ሐማሴኖች››በሚል ርዕስ በመጋቢት 1942
በሚስጥር የተላከ ቴሌግራም በቁጥር 1330/42 በ‹‹የኢትዮጵያ
ንጉስ
ነገሥት መንግሥት አልጋ ወራሽ መርዕድ አስፋ ወሰን ኃይለ
ሥላሴ ልዩ ጽህፈት ቤት››የተፃፈ ነበር።
የተፃፈውም ‹‹ለፊት አውራሪ ክፍሉ ዳዲ›› ነበር። በደብዳቤው
ውስጥ☞ ‹‹… ብዙ እስላሞች ውደ
ውጭ ይሄዳሉ ማለት ስለተሰማ ጉዳዩን በሚስጥር ተከታትለው
ሆኔታውን እንዲያሳውቁኝ ከልዑል ጌታዬ መታዘዙን በማክበር
አስታውቃለሁ›› ሲል ያስረዳል።
የአፄው መንግሥት ሙስሊሙን ከውጭ ጉዞ ለማገድ የተጠቀመው
አንዱ ስትራቴጂ የዜግነት መብት የሆነውን የመጓጓዣ ፓስፖርት
መከልከል ነበር።
ሆኖም ሙስሊሙ ያለ ፓስፖርት በእግርም ቢሆን ድምበር አቋርጦ
መሰደዱን አላቆመም ነበር።
ወደ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ሳዑዲ ዐረቢያ ወዘተ ይሰደድ ነበር።
ለምሳሌ☞ ወደ ግብጽ ያለ ፓስፖርት የተሰደዱ ሙስሊም ወጣቶች
ሰው አገር የመማር እድል ፍለጋ ሲንከራተቱ ነበር።
በግብጽ አሌክሳንደሪያ ለሚማሩ ክርስቲያን ተማሪዎች ፓስፖርት፣
ቀለብና ድጋፍ ሲደረግ ለሙስሊሞቹ ግን የዜግነት ፓስፖርት ሁሉ
ተነፈጉ። በአንድ ወቅት ለእኛ ለሙስሊሞቹ ‹‹ፓስፖርትና ድጋፍ
የማግኘት ወግ ቢደርሰን›› ብለው በግብጽ ወደሚገኘው
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሄደው ጠየቁ። ነገር ግን ፀረ- ሙስሊሙ
የኃይለ ሥላሴ መንግሥት ምላሹን ፓስፖርትና ድጎማ ሳይሆን
የፖሊስ ጥቃት አደረገው። ከአገር ያሳደዳቸው መከራም በዚያ
ተከተላቸው።
በኤምባሲው ከሳሽነት ሙስሊም ተማሪዎች በፖሊስ ታፍሰው
ታሰሩ። ተማሪዎቹ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ለአዝሀር ዩኒቨርሲቲ
አስተዳደር አቤት አሉ። ጉዳዩን ሐጅ በሽር ዳውድ
እንዲህ ያወሱታል፡- ‹‹በዚህን ጊዜ ሕገ ወጥ ተግባር ያልፈፀሙ
መሆኑ ተረጋግጦ የተያዙት ተማሪዎች እንዲለቀቁ አስተዳዳሪው
ከመሥሪያ ቤቱ አንዱን ባለሥልጣን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ልኮ ጉዳዩን
እንዲያጣራ ይደረጋል። ተማሪዎቹ የፈፀሙት ወንጀል ባለመኖሩ
በመልእክተኛው ዋስትና እንዲለቀቁ ሲደረግ ማህደር ተከፍቶ
‹ወንጀለኛ ነህ አይደለህም?› የሚል ጥያቄ ለእያንዳንዱ ቀርቦ
‹አይደለሁም› የሚል መልስ ስለሰጡ የዚያኑ ቀን ተለቀቁ።
ከታሳሪዎቹ አንዱ ‹ወንጀለኛ ነኝ› የሚል መልስ ሰጠ።
‹ምንድን ነው ወንጀልህ?›ሲሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ግፈኛና
እስላም የሆኑትን ዜጎቹን መብት የነፈገ መሆኑን እያወቅኩና
እያመንኩበት እርዳታ ጥየቃ ወደ ኤምባሲው መሄዴ ነው ወንጀሌ!
ሌላ ወንጀል የለኝም!› የሚል መልስ ሲሰጥ እዚያ የነበረው ሁሉ
በኢትዮጵያ እስላሞች ላይ የሚፈፀመው በደልና ግፍ በሃገራቸው ላይ
የተወሰነ ብቻ ሳይሆን ውጭ ሃገር ድረስ እየተከታተለ
እንደሚያሰቃይ ስለተረዱ ልጆቹ በርህራሄና ከሃዘኔታ ጋር እንዲለቀቁ
ተደርጓል።››
አፄ ሀይለስላሴ በአምስቱ የጣሊያን የወረራ ዘመን የሀገሪቱን ሀብትና
ንብረት ጭኖ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ እንግሊዝ ተጉዟል፥አውሮፓና
አሜሪካ እያካለለ ደስታ ሸምቷል::በተቃራኒው የባንዲራ
መዋረድ፣የሀገር ድንበር መደፈር ያስቆጣቸው ጀግኖች ለሉአላዊነቷ
ደማቸውን ገብረውላታል፥ህይወታቸውን ሰውተውላታል::
በቀደመው አድዋ የጣሊያን ወረራ የጦር አዝማች
የነበሩት ጀግናው ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) አጼ ሀይለስላሴ
ለስልጣኑ ፈርቷቸው በቁም እስረኛነት አግልሏቸው ነበር::
አፄው ህዝብና ሀገር ጥሎ ወደ እንግሊዝ ሲበር ግን ባልቻ ሳፎ
(አባነፍሶ) ለሀገራቸው ክብር እጄን ለጠላት አልሰጥም ብለው
ተታኩሰው ሞተዋል::
ከሁለተኛ የአለም ጦርነት መፈንዳት ተያይዞ በእንግሊዝ እርዳታ
በጀግኖች አባቶቻችን ደም ጣሊያን ተሸንፋ ስትወጣ አጼ ሀይለስላሴ
አስቂኝ ድራማ ሰራ:: ብሄራዊ ጀግና ተሰኝቶ ወደዙፋኑ
ተመለሰ::
በጣሊያን ወረራ ሚስቱ ተገድላ ልጁ በጠላት እንደምርኮ ተይዞ እጁን
እንዲሰጥ ሲጠየቅ ከሀገሬ አይበልጡብኝም ብሎ ጣልያንን በጀግንነት
የተዋጋው በላይ ዘለቀ በአጼ ሀይለስላሴ
ሸምቀቆ የዛሬው ሲኒማ ራስ (አዲስ አበባ) አካባቢ
ተሰቀለ::ሀገርና ህዝብ በጦርነት ጊዜ ጥሎ በመኮብለሉ ሊሰቀል
ይገባው የነበረው አጼ ጀግኖችን ሰቀለ፥አሰረ፥አሳደደ!
በርግጥም
☞“ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የሚለው ስንኝ በምክንያታዊነት
የሚሰማበት ዘመን ነበር::
አጼ ሀይለስላሴ በዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ በጥብቅ ሀይል ለመግዛቱ
እንደምክንያት ከሚቀመጡ ነጥቦች ከላይ የተመለከትነው ጭካኔው
ይገለጻል::
ኢትዮጵያ ስትጠራ ሀይለስላሴ ብቻ እንዲዘከር ይፈልግ ነበር:: ይህን
የሚያጠለሽ ሁኔታ
በየትኛውም መስዋእትነት ያስወግድ ነበር:: እድሜ የጠገቡ ሰዎች
የአበበ ቢቂላን በመኪና አደጋ አካለ ስንኩል መሆንና ተከትሎም
መሞት ከሀይለስላሴ ሴራ የሚያያይዙት ለዚህ ነው::
ያልዘሩት አይታጨድምና ሌሎችን ለዙፋኑ እንደገደለ የራሱ ልጅ አልጋ
ወራሽ አስፋው ወሰን ታናሽ ወንድሙ ልኡል መኮንንን በመኪና አደጋ
አስገድሏል::”ከጂን ከጂ ይክዳው ነውና ” አጼው
ብዙዎቹን ከድቶ ዙፋን ላይ እንደመቀመጡ በታህሳስ ወር 1953
የነጄኔራል መንግስቱ ንዋይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ልጁ አስፋው
ወሰን ተባባሪ ነበር::
አጼ ሀይለስላሴ በህይወቱ እያለ በርካታ ልጆቹና ሚስቱ እቴጌ መነንን
ቀብሮ በሀዘን ኖሯል::
አጼው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአደንዛዥ እጽ የነፈዙ የጃማይካ ራስ
ተፈሪያን በሚያስቡት መልኩ ከሰማይ የወረደ ቅዱስ መንፈስ
አድርገው እንዲያስቡት ጥረት አድርጓል::
….ቀን ጥሎት ሌባ እየተባለ ከቤተመንግስት እስከወጣባት እለት
ሀገርና ዜጋ ሲቦጠቡጥ በጥንቆላ፣ለሰይጣን በመገበር ኖሯል::
⑧. ☞ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲጠራጠር ማድረግ
በአፄው አገዛዝ ዘመን ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲጠራጠር
በርካታቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ድርጊቶች ሲፈፀሙ ነበር።
ስለ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ መንግሥቱ ሲነገር ሆን ተብሎ ከክርስትናና
ከቤተክህነትጋር ብቻ በማስተሳሰር ‹‹አትዮጵያዊ›› የሚለው
ከ‹‹ክርስቲያን›› ቃል ጋር እኩል እስከ መሆን ደርሶ ነበር።
ከሕገ መንግስቱ አንስቶ መንግስታዊ መዋቅሩ ሁሉ ለኢትዮጵያውያን
ሁሉ ሳይሆን በቤተክህነት ፍላጎት ስር ተጠፍሮ ነበር።
☞ ሙስሊሞችን ‹‹ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች› › ሳይሆን
‹‹ በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች›› እያሉ መጥራት የተለመደ
ተግባር ነበር።
ይህን የሚያደርጉት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በእንግድነት
በሀገሪቱ የሚኖሩ ባዕዳን ለማስመሰል እና ሀገራዊ ስሜት
ከውስጣቸው እንዲንጠፈጠፍ ለማድረግ በማለም ነበር።
☞ በ1966 ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ካቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ
አንዱ ይህ ነጥብ ነበር። እንዲህ ብለው ነበር፡-
☞ ‹‹በኢትዮጵያ የሚገኙ እስላሞች እየተባለ በሬድዮም ሆነ
በቴሌቪዥን ወይም በማንኛውም የመገናኛ ዘዴዎች የሚነገረው
አነጋገር በኛ
በኢትዮጵያውያን እስላሞች ላይ እንደ ውጭ አገር ኮሚኒቲዎች
በገዛ አገራችን የባእድነትን ስሜት ስለሚፈጥርብን ይህ አይነቱ
አነጋገር ፈፅሞ እንዲቀርና ምናልባትም ስለኛ የሚነገር ነገር
ቢኖር
በነዚሁ የመገናኛ ዘዴዎች ‹ኢትዮጵያውያን እስላሞች› ተብሎ
እንዲነገር እንፈልጋለን። ይህንም ለማለት ካሰኙን ምክንያቶች
አንዱ
☞ኢትዮጵያ ማንኛውም ሃይማኖት ከመግባቱ በፊት የነበሩ ዜጎችም
ኢትዮጵያውያን ተብለው ሲጠሩ የቆዩባት እንደመሆኗ መጠን የተለያዩ
እምነቶች ስለገቡ ብቻ በኢትዮጵያውያን መካከል ልዩነት ማድረግ
ስለማይገባ የልዩነት መንፈስ ሊያሳድሩ የሚችሉትን የቃልም ሆነ
የሥራ ድርጊቶች
እንዲቀሩ ጨምረን ለመጠየቅ ነው›› ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።
Click ☞ bit.ly/1PBnJ4l
click☞ bit.ly/1QeueX3
ይህ ስትራቴጂ ያሳደረው ተጽእኖ ምን ያህል እንደሆነ በአሁኑ ሰዓት
በግልጽ የምናየው ነው።
ሙስሊሙን በሀገሪቱ ጉዳይ ታዛቢና የዳር
ተመልካች አደርጎታል። ዘማች አብደላ ሃሰን ‹‹አስጨናቂው
እልፈት››በሚል በአፄው ውድቀት ማግስት በቋጠረው ስንኝ
ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊነቱን ወደ መጠራጠር ሁሉ ደርሶ እንደነበር
ይገልጻል።
እንዲህም ይላል፡-
‹‹በተለይ እኛ እስላም የተባልነው
ንጉሱ ሲወጣ ጥንቱን ያልታደልነው
መኖር አስመርሮን ማሰቡ ከብዶን
የመሞት የመኖር የአብዮት ልዩነት ሳይታወቀን
ኢትዮጵያነትን ጠርጥሮ አይናችን
ሌላ አገርን ሲመኝ ኖሯል ቀልባችን››
⑨. ☞ክርስቲያኑን ማጠናከርና ሙስሊሙን ማዳከም
የአፄው መንግሥት ክርስቲያኑን ለማጠናከር ከመንግሥት በጀት
ከፍተኛ ወጪ በማድረግ በርካታ ተግባራትን ይፈፅም ነበር።
ሙስሊሙ ከሚገብረው ግብር ጭምር የሚገኘው የሀገር ኢኮኖሚ
ሳይቀር የኦርቶዶክስን እምነት ለማጎልበት ውሏል።
☞በርካታ ሕንፃዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሃይማኖት
ተቋማት፣የትምህርት ማዕከላት ተመስርተውበታል።
የቤተክህነት የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ወጪ
ሲተዳደር ነበር።
የሥላሴ ኮሌጅን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ተቋማት በሀገሪቷ
ገንዘብ ተገንብተዋል።
በተቃራኒው ሙስሊሙ ይህን እድል ሊያገኝ ቀርቶ
በገዛ ገንዘቡ እንኳ መስጂድ መሥራት ፈተና ሆኖበት ነበር።
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በቢሮክራሲ በመቆላለፍ እንዲዳከም
ተደርጓል።
☞በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ውስጥ
በማህደር ቁጥር 2396/02/3 የተመዘገበ የአንድ ሙስሊም ጽሑፍ
እንዲህ
ይላል፡-
‹‹እስላምና ክርስቲያን በነገር ቢገጥሙ ለክርስቲያኑ ነገሩ ቶሎ
ይፈጸምለታል። ለእስላሙ ቀን በመቅጠር
ያዳክሙታል።ሲደክም ገንዘቡንና ጉዳዩን ትቶ ይሄዳል።
በእስላሞችና በክርስቲያን ያለ ስለመስጂድ ሥራ እና
ስለቤተክርስቲያን ሥራ በአዲስ አበባ ከሁለት መስጂድ በስተቀር
ሌላ አይገኝም።የክርስቲያን ቤተክርስቲያኖች ግን በከተማው 89
ሲሆኑ ሁሉንም መንግሥት
ነው የሰራው። በእስላሞችና በክርስቲያን ገንዘብ ለቤተ
ክርስቲያን የሚያስፈልግ ሁሉንም መንግሥት ይከፍላል፤
ለመስጂዱ ግን ለኮረንቲ ሳይቀር ከኪሳችን እንከፍላለን።›› ይህ
ሙስሊሙን
በማዳከም ክርስቲያኑን የማደርጀት ስትራቴጂ በሚገባ የተተገበረና
ጉልህ ውጤትም ያስመዘገበ ነበር።
የአፄው መንግሥት ክርስትናን ለማጠናከርና በተቃራኒው ደግሞ
ኢስላምን ለማዳከም የሀገሪቱን ሀብት አሟጧል። በርካታ
ተግባራትንም ፈጽሟል።
ሙስሊሙ ኅበረተሰብ በወቅቱ በአዲስ አበባ የነበሩትን ሁለቱን
መስጂዶች እንኳን ለማጠናከር በርካታ መሰናክሎች ገጥመውት
ነበር።
☞ ለአብነት ያህል አንዋር መስጂድ ከተሰራ በኋላ ለህንፃ ተቋራጩ
የሚከፈል ገንዘብ ጠፍቶ መስጂዱ
ተከሷል። ፍርድ ቤትም መስጂዱ እንዲዘጋ ወስኗል። በአንዋር
መስጊድ ኮሚቴ ‹‹ታላቁ የአንዋር መስጊድ በአዲስ አበባ››
በሚል ርዕስ በራስ ተፈሪ (ኃይለ ሥላሴ) ውድቀት ማግስት የተጻፈው
መጽሐፍ እንዲህ ይገልጻል፡–
‹‹መስጊዱ አል-አንዋር ተሰርቶ እንዳለቀና ለጸሎት አገልግሎት
ከዋለ በኋላ የሕንፃው ሥራ ተቋራጭ መስጊዱን ሰርቶ
ሲያስረክብ ቀሪ የነበረው የ16.000 (አሥራ ስድስት ሺህ ብር)
ሒሳብ ስላልተከፈለና የተወሰነ የጊዜ ገደብ ስላለፈ ከፍርድ ቤት
በመጣው ትዕዛዝ መሠረት መስጊዱ እንዲዘጋ አድርጎት ነበር።
ምንም እንኳን ነዝሩ በዚያን ጊዜ መስጊዱ ምንም ገንዘብ
የሌለው መሆኑን ለሥራ ተቋራጩ ቢያስገነዝብም መጠነኛ ጊዜ
እንኳ ለመስጠት ተቋራጩ ሳይፈቅድ ቀረ። ከዚህ በኋላ
የመስጊዱ አስተዳዳሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ
አዛውንቶችና ሽማግሌዎች
ተሰብስበው ምክር ካደረጉ በኋላ ይህ በፍርድ የተወሰነብን
ገንዘብ ከምንም ይምጣ ከምን በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲከፈል
ተወሰነ። ቢሆንም
ይህ ገንዘብ በዚህ ሰዓት ውስጥ ባይከፈል ደግሞ ከመስጊዱ
መሬት ቀንሰው በሀራጅ እንዲሸጥ፣ ለተቋራጩ የሚከፈል
መሆኑን ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ አሳሰበ።››
የሆነው ሆኖ የአንዋር ናዝር የነበሩት ሐጂ አቡበከር ሸሪፍ አስቸኳይ
ስብሰባ ጠርተው ሙስሊሙን አወያዩ። የሙስሊሙ ዓይን የነበረው
ታላቁ የአንዋር መስጂድ ከሚዘጋ በሚል ሙስሊሙ ያለውን ሁሉ
አወጣ።ተሳክቶም የአንዋር መስጊድ 16 ሺህ ብሩን ከሙስሊሙ
ተበደረ። ብድሩን የሰጡት ሐጂ ራህመቶ ሙክታር (5 ሺህ)፣ ሐጂ
አብዶ አርሲ (2 ሺህ)፣ ሐጂ ዑመር ኢብራሂም (1ሺህ)፣ ሐጂ
ሙዘይን ኡስማን (1 ሺህ)፣ ሐጂ አቡበከር ሸሪፍ (2 ሺህ)፣ ሐጂ
ሙሐመድ ጀማል (3 ሺህ)፣ ሐጂ ጀማል ሐሰን (1 ሺህ) እና ሐጂ
በሽር ገዳ (1 ሺህ) ነበሩ። አላህ ይቀበላቸው።
ጀግኖች አባቶቻችን ለሀገር ሉአላዊነት ወራሪ ኢጣሊያን ሲፋለሙ
ከእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ደቡብ ምእራብ 156 ኪሎሜትር ርቀት
በምትገኘው ውብ የሰመርሴት ከተማ ባዝ (Bath,Somerset) አንድ
ኢትዮጵያዊ በውድ ቪላው እየተዝናና የህይወት ታሪኩን ይጽፍ ነበር::
በረጅም ግድግዳ በተከበበው ባለ አስራ አራት ክፍል ቪላው ይከትብ
የነበረው ግለሰብ ተራ
የሚባል አይደለም::ሀገሩ በጠላት ተወራ ነፍሱን ለማዳን ከነቤተሰቦቹ
የሸሸ የታላቋ ኢትዮጵያ ንጉስ ሀይለስላሴ ነበር!
ቀደምት ነገስታትም ሆኑ ከኋላው የተከተለው ወታደራዊ ገዥ ሀገር
በጠላት ስትደፈር ጦር ሜዳ ዘልቀው ሲያዋጉ እንጂ እግሬ አውጭኝ
ብለው ሲሸሹ ታሪክ አልመዘገበም::
የሆነው ሆኖ አጼ ሀይለስላሴ በተቀማጠለ ድሎት ከባዝ መጻፍ
የጀመረው መጽሀፍ ርእስ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” (My Life
and Ethiopia’s Progress) በሚል ርእስ የተዘጋጀ ባለሁለት ቅጽ
ነው:: 90 ሺህ ቃላት ከተጠቀመባቸው ሁለቱ
መጽሀፎች
☞አንደኛው ቅጽ ከንጉሱ ውልደት 1884 አመት እስከ ጣሊያን ወረራ
1928 አመት የተመረኮዘ ሲሆን፥
☞ሁለተኛው ቅጽ ደግሞ ጣሊያን ሀገራችን ወርራ የቆየችባቸው
1928-1933 አመት የተፈጸሙ ሂደቶች ያላቸውን ያተተበት ነው::
የመጽሀፉ ሁለቱም ቅጾች አፄው ከሽሽት ወደሀገር ከተመለሰ በኋላ
በታዋቂ ጸሀፊያን ተሞርደዋል:: ንጉሱ በደርግ ሊባረር አንድ አመት
ሲቀረው
በ1965 አመት መጽሀፎቹ በአማርኛ ቋንቋ ታትመዋል::
የአጼ ሀይለስላሴ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” መጽሀፍ አጠቃላይ
ይዘት አጼው ያለፈባቸው ወንጀሎቹን በማለባበስ ራሱን ከፍ አድርጎ
ለማሳየት የደከመበት ነው::
ጣልያን ወደ ኢትዮጵያ እግሯን ስታስገባ የቤተመንግስት መሳፍንትና
መኳንንት በአጼ
ሀይለስላሴ ጉዳይ የሀሳብ ልዩነት ነበራቸው::ንጉሱ ጎሬ ከተማ
ተቀምጦ ያዋጋ ወይስ ከቤተሰቦቹ ተከትሎ ወደውጭ ሀገር ይሂድና
በዚያው ለአለም መንግስታት የጄኔቩ ስብሰባ አቤቱታ ያቅርብ?
በሚለው ክርክር ተነስቷል:: ብላታ ተክሌ ወልደ ሀዋርያትና ሌሎች
በርካታ ጉምቱ መሳፍንቶች የንጉሱን ከሀገር መውጣት በአጽንኦት
ተቃውመዋል::
እነዚህ ሰዎችን ጨምሮ ፥በጣልያን ወረራ
ከሀገር በመሸሹ፣ከነጻነት በኋላ ወደሀገር ሲመለስ ደግሞ እንደነበላይ
ዘለቀ አይነቱን ጀግኖች በመግደሉ ተቃውመው የጻፉ በውጭ
የሚኖሩ ተራማጅ ኢትዮጵያውያን ጸሀፊዎች ተቀባይነት
እንዳይኖራቸው ለማጠልሸት አጼው ከመጽሀፉ መግቢያ
የሚከተለውን አስፍሯል::
“በጠንካራ መሰረትና በእብነበረድ የተገነባ ቤት የዝናብ
መዝነብ፣ሀይለኛ ጎርፍ ወይም ሀያል አውሎ ንፋስ
አያፈርሰውም::አንዳንድ ሰዎች ባለማወቅ፣ በስህተት ወይም
በቅናት ተነሳስተው ስለኔ የህይወት ታሪክ እውነት አስመስለው
ለመጻፍ ሞክረዋል::ነገር ግን ሌሎችን ለማሳመን ቢሞክሩም
እውነትን ካለችበት መነቅነቅ አይችሉም::”
“A house built on granite and strong foundations,
not even the onslaught of pouring rain, gushing
torrents and strong winds will be able to pull down.
Some people have written the story of my life
representing as truth what in fact derives from
ignorance, error or envy; but they cannot shake the
truth from its place, even if they attempt to make
others believe it.”
አጼ ሀይለስላሴ ጥቅምት 23/1923 የንግስና ዘውድ ሲደፋ
ከየአለማቱ ለመጡ እንግዶች ለተዘጋጀ ስጦታ የባከነው 3 ሚሊዮን
ዶላር ከወቅቱ የሀገሪቱ አቅም አንጻር በጣም ከፍተኛ
ነበር::
ከባሪያ ስርአተ ማህበር ብዙም ፈቅ ያላለችው የቆረቆዘች ሀገር ንጉስ
ሀይለስላሴ የበለጸጉ ካፒታሊስቶችን በከበረ ድንጋይ ስጦታ
ማስደመሙ እጅግ የከፋቸው ሀገር ወዳዶች ነበሩ::አጼው
ስርአተ ንግስናውን እንዲባርክለት ጋብዞት ለቀረበት የአሜሪካ ጳጳስ
በወርቅ ሽፋን የተለበጠ መጽሀፍ ቅዱስ በስጦታነት እንደላከለት
ስንረዳ በአርባ አራት አመት አስተዳደሩ ሀገራችን ምንኛ በብኩንነት
እንዳወደማት መገንዘብ ይቻላል::
ድርቅ የተለያዩ የሀገሪቱን ክፍሎች በተለይ ወሎን መትቶ ዜጎች
በረሀብ ሲቆሉ አጼ ሀይለስላሴ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ስዊዝ
ባንክ በግል ሂሳቡ አስቀምጦ ነበር::
ህዝብን በቸነፈር፣ሀገርን በድህነት ሲያሽ የነበረው ‘ንጉሰ ነገስት’
ሀይለስላሴ ከአርባ አመት በፊት ወደማይመለስበት ቢሄድም
ቅሉ፥በዘረፈው የሀገር ሀብት የሚምነሸነሹ ዘመድ፣ቤተሰብ…
በተኳለ ቀለም፣ባማረ የሬጌ ዜማ ታሪኩን የተጋቱ የዚህ ዘመን
ትውልዶች የከሳውን አስብተው፣ ጥቁሩን አንጥተው ሊያወጉን
ይፈልጋሉ:: ሆኖም እኛ በሀገራችን፣በሀይማኖታችን የሰራውን አስከፊ
በደል በወጉ ተረድተናልና አንሞኝም::
ሀይለስላሴ በቴዲ አፍሮ ያማረ ቅላጼ እንደተንቆለጳጰሰው አይደለም
ለኛ!
በማሪዋና የነበዙ ራስታዎች በሬጌ እንደሚያሸረግዱለት ቅዱስ
ሳይሆን
ለሰይጣን የሰው ህይወት ይገብር እንደነበር ነው የምናውቀው!
⑩. ☞ኢስላምና ሙስሊምን ማጥላላት
የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት እንደቀደምት አፄዎች ሁሉ
ከተጠቀማቸው ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ ኢስላምንና ሙስሊሙን
ማጥላላት ነበር። ይህ ስትራቴጂ እስልምናንና ሙስሊሙን የሀገር
ስጋት አድርጎ ማቅረብን ያቀፈ ነበር።
ሙስሊሙ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ በታሪክ በደል ሲያደርስ የኖረ
አስመስሎ በማቅረብ ‹‹ስጋትነታቸውን›› ያሳዩ ነበር።
click☞ bit.ly/1QeueX3
☞ለህጻናቱ፣ ለፖለቲከኛውና ለጦር ሠራዊቱ ሳይቀር ኢስላምንና
ሙስሊሙን የኢትዮጵያ ስጋት
አድርገው ያቀርቡ ነበር።ሙሐመድ ሰኢድ ኢብራሂም በ 1968
እንዲህ ሲል ገልጾት ነበር፡- ‹‹ኢትዮጵያውያን እስላሞች
በክርስቲያን
ወንድሞቻቸው ላይ ከባድ የግፍ ድርብ ጭካኔና አመጽ የፈጸሙ
በማስመሰል፣የሐሰት ቱልቱላ በመንፋት በህፃናት አእምሮ
ተቀርጾ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማረማመዱ እንዲኖር
በመጽሐፍ
እያተሙ ለአገር ልማትና እድገት፣ ህብረት ታላቅ ቁም ነገር
የፈጸሙ በማስመሰል (ይጽፉ ነበር።)››
የማጠልሸቱ ተግባር በዚህ ብቻ ሳይወሰን ኢስላምንና ተቋማቱን
በቀጥታ ዒላማ ያደረጉ ተግባራትም ተፈጽመዋል። ለአብነት ያህል
የሸሪዓ ፍርድ ቤት ተግባርና ፍርድ መሀል ጣልቃ በመግባት፣
ሙስሊም ያልሆኑ ሠራተኞችን በመመደብ፣ ፍርድ ቤቱን ደካማና
ፍትህ የሚጠመዘዝበት በማድረግ ሰው እንዲጠላው ሲያደርጉ ነበር።
በአፄው ውድቀት ማግስት የሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ሐጂ
በሽር ዳውድ እንዲህ ሲሉ በወቅቱ በቢላል መጽሔት ጸፈው ነበር፡-
☞‹‹እንዲያው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ
ለሃይማኖታቸውና ለአገራቸው የሚቆረቆሩ ሁሉ ‹ይህ ፍርድ ቤት
(የሸሪዓ ፍርድ ቤት)የተቋቋመው የኢስላም ሃይማኖትን ለመጠበቅ
ሳይሆን ሕዝቡ ራሱ ቀስ በቀስ ሃይማኖቱን ጠልቶ እንዲተው ረቂቅ
በሆነ ጥናትና ተንኮል የተመሠረተ ፍርድ ቤት ነው› በማለት
እያጉረመረሙ ለብዙ ዘመናት ከፍ ባለ ሀዘን ተውጠው መኖራቸው
የማይካድ ነው።››
⑪.☞ሙስሊሙን መሪ ማሳጣት
የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት አንዱ ስትራቴጂ ሙስሊሙን በትክክል
የሚወክል አካል እንዳይኖር ማድረግ ነበር።
ለሙስሊሙና ኢስላም የሚሠራ አንደ ቤተክህነት መሪ ድርጅት
እንዳይኖር አድርጎ ነበር። ሙስሊሞች በ1966 ለመንግሥት
ካቀረቧቸው ጥያቄዎችአንዱ የነበረው ይህ ነበር።
☞‹‹በሕገ መንግሥቱ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ማኅበር የማቋቋም
መብቱ የተጠበቀ ነው ቢባልም በእስልምና ሃይማኖት የተቋቋመ
ማኅበር
ባለመፈቀዱና ከዚህም የተነሳ ኢትዮጵያውያን እስላሞች
በኢንተርናሽናል ደረጃ በሚካሄዱ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች
ስብሰባዎች
እንዳንካፈል እና ከጊዜው አስተሳሰብ ጋር እንዳንራመድ አድርጎናል››
ሲሉም ጠይቀዋል።
ቤተክህነትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲያጠናክሩ ሙስሊሙ ግን
በሕገ መንግስቱ የተፈቀደውን ነፃ የሃይማኖት ድርጅት ማቋቋም እንኳ
ተነፈገ።
የአፄው መንግሥት ይህን ሁሉ ግፍ እየፈጸመም ‹‹ሃይማኖት የግል
ነው። ሀገር ግን የጋራ ነው›› የሚል ብሂል በአደባባይ ይደሰኮር
ነበር።
በአፄው ጊዜ ‹‹ሰላማዊ ማኅበር›› በሚል መጠሪያ የሙስሊሞች
መሪ ድርጅት ተቋቁሞ ነበር። ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በኋላ በአፄው
መንግሥት ሰርጎ ገቦች ተጽእኖ እንዲፈርስ ተደርጓል።20 የሙስሊሙ
ጉዳይ በሕግ ሳይሆን በሰርጎ ገቦችና በአፄው
ግለሰቦች የግል ቁጥጥር ስር በጉልህ ወድቆ ነበር።
የሙስሊሞች ሥራ በዒድ ቀናት ንጉሡ ዘንድ በመሄድ ‹‹እንኳን
አደረሰዎ›› ማለት ብቻ ሆነ።
ሙስሊሙ በሕጋዊ መንገድ የተፈቀደለት ሐጅ ብቻ ሆነ ።
እርሱም ቢሆን ከዓለም ሙስሊም ስብስብ መሀል ኢትዮጵያውያኑ
ቢቀሩ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው በማለም ነበር።
ከሐጅ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን በሐጅ ላይ የኃይለ ሥላሴ መንግሥት
ለመስሊሙ መልካም እንደሆነ እንዲናገሩ ይመከሩ ነበር።
የሙስሊሙ መብትና ነጻነት በግለሰብ እጅ ወደቀ።
ይህንን ሁኔታ የወቅቱ የአንዋር መስጅድ ኮሚቴ እንዲህ
ይገልጹታል፡- ‹‹በተለይ በ1942 ዓ.ም ከተደረገው የመንግሥት
ሹም ሽር በኋላ ከፍተኛውን ሥልጣን ይዘው የነበሩት አቶ
መኮንን ሀብተ ወልድ የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች ጉዳይ ሁሉ
በቀጥታ
በሳቸው ቁጥጥር ስር እንዲውል አስወስነው የእስላም ኮሜቴ
ጽ/ቤት ከነበረበት ከሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ወደ አገር ፍቅር
ማኅበር እንዲዛወር አደረጉ። ወዲያው የእስላም ኮሜቴ ጽ/ቤት
እንዲሻርና ሥልጣንም እንዳይኖረው፣ ከቀረው የመንግሥት
መስሪያ ቤት ጋር ግንኙነት እንዳያደርግ ከልክለው ሲወስኑ
ግንኙነቱን በቀጥታ ከራሳቸው ጋር እንዲሆን አደረጉ። በዚህም
ምክንያት ኢትዮጵያውያን እስላሞች ሊኖራቸው የሚገባቸውን
መብትና ሙሉ ነጻነት በመግፈፍ እና ወደፊትም ብሔራዊ
እርምጃዎችን እንዳይቀላቀሉ…..ከፍተኛ ተጽዕኖ እና በደል
ከማድረጋቸውም በላይ አድራጎቱ የ‹ከፋፍለህ ግዛ› ዘዴ
እንደነበረ ከማንም የተሰወረ አይሆንም።››
ሙስሊሙን መሪ የማሳጣት ስትራቴጂን በዚህ መልኩ የተገበረው
የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ቀብር አምልኮ ላይ የነበሩት ሰዎች
ሙስሊሞችን
እንዲመሩ ለማድረግ ጥረዋል።የዲን መነቃቃት ያላቸውንና
ለሙስሊሙ መብት ተቆርቋሪ የነበሩትን ሲያሳድዱ ኖረዋል።
በተቃራኒው ቀብር ከማምለክ ውጭ ስለሙስሊሙ
መብት ግንዛቤ የሌላቸውን፣የኢትዮጵያን ተጨባጭ የማይረዱትን
በገንዘብ በመርዳት ሌሎች ዓሊሞች እንደነርሱ እንዲሆኑ ይፈልጉ
ነበር።
ለምሳሌ
☞አፄ ኃይለ ሥላሴ ድሬ ሼኸና ሁሴንን ሊያጠናክር ሲደክም ነበር።
☞እ.ኤ.አ በ1962 ድሬ ሼኸና ሁሴንን
ጎብኝቷል።የገንዘብ ድጎማ አድርጓል። ለድሬ ሼኸና ሁሴን መንደር
መሪዎች በዓመት አንድ ሺህ ብር ደሞዝ ሲመድብ 235 (ሁለት መቶ
ሰላሣ አምስት) ጋሻ መሬቶቻቸውን ከግብር ነጻ አድርጎላቸዋል።
ምንም እንኳ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ስትራቴጂዎች እጅግ በርካታ የነበሩ
ቢሆንም ለዛሬው በዚህ ይብቃን።
ለበለጠ መረጃ Click ☞ bit.ly/1PBnJ4l
click☞ bit.ly/1QeueX3
=======ተፈጸመ==========www.or-more.com

Friday, January 11, 2019

የስልጤ ህዝብ ታሪክ

የስልጤ ህዝብ ታሪክ

ክፍል  ሁለት

#የስልጤ ገራዳዊ ሥርዓት

ኢማም አህመድ በተሸነፈበት ዘመን ብዙ የሕዝቦች (በተለይም የኦሮሞ)

እንቅስቃሴ ተከስቶ ነበር። የኢማሙ የጦር አበጋዞች ከነሠራዊታቸውና

የእስልምና ሚሺነሪዎች (ዳኢዎች) በኡምናን፥ በወለኔ፥... አካባቢዎች

ሰፍረው ነበር። እነዚህ ቡድኖች ከሐረር ጋር የነበራቸው ግንኙነት በአርሲዎች

(አርሲዎች ስልጤን ‘ሀደሬ’ ብለው እንደሚጠሩት ልብ ይሏል) በመቋረጡ

ወይም በሌላ ምክንያት ወደ ሐረር ሳይመለሱ ቀሩ። ይህ ሌላ ታሪካዊ ሁኔታን

ፈጠረ።

ወደ ሐረር ያልተመለሱት የኢማም አህመድ ግራኝ የጦር አበጋዞች ኀይላቸውን

አጠናክረው ገራዳዊ ሥርዓት (አካባቢያዊ መንግሥት) መሠረቱ። እነዚህ

መሪዎች ግን ሱልጣኖች ሳይሆን ገራዶች ይባሉ ነበር።

የመጀመሪያው የገራዳዊ ሥርዓት ማዕከል ኡምናን (ኡምናን አዘርነት ውስጥ

የምትገኝና የሀጂ አሊዬ መካነ መቃብር የሚገኝባት ታሪካዊ ሥፍራ ናት)

ሲሆን መሪውም ሀዲ ገራድ (ሀጂ) አሊዬ ኡመር ነበሩ። ስልጤ የሚለው

ስምም በዚያ ገራዳዊ ሥርዓት ውስጥ ተፀንሶ ያደገ በመሆኑ ገራዳዊው

ሥርዓት ለስልጤዎች ልዩ ትርጉም አለው። ምክንያቱም ‘ሱልጣኔት’

የሚለውን የሀዲያ ግዛት አሻራ የያዘ በመሆኑና ራሳቸውን ከሌላው ‘ሀዲያ’

የሚለዩበት በመሆኑ ነው። ስልጤ የሚለው ቃል ሱልጣኔት ከሚለው ቃል

የመጣ ነው። ስልጤ የሕዝቡ ብቻ ሳይሆን የአገሩም መጠሪያ መሆኑ መዘንጋት

የለበትም።

ይህ ገራዳዊ ሥርዓት እስከ 1881 ቀጠለ። እዚህ ጋ አንድ ነገር ለናስታውስ

ፈለግን፤ ይሀውም ስልጤ የነባር ሕዝቦችና የመጤዎች ድብልቅ መሆኑን ነው።

ነባሩ ሕዝብ ሀገር (ባንዳንድ ቦታ ዠራ) ተብሎ ሲጠራ መጤዎቹ አጃሞ

በመባል ይታወቃሉ።

#የሸዋ መንግሥት መፈጠር

የሸዋ መንግሥት መፈጠር በተለይ የአጼ ምኒልክ ወደ ደቡብ መስፋፋት

በእነአምደ ጽዮንና በሐዲያ ሱልጣኖች መሃል የተከሰተውን ዓይነት ችግር

በምኒልክና በስልጤ ገራዶች መሃል ፈጠረ። በዚህም የተነሣ የሙስሊሞችና

የምኒልክ ጦር ተደጋጋሚ ጦርነቶችን አደረጉ (ከሐሰን እንጃሞ ጎን ስልጤዎች

ተሰልፈው ተዋግተዋል)።

በመጨረሻም ጋሮሬ ወንዝ አካባቢ በተደረገ ጦርነት የስልጤ ገራዶች ለምኒልክ

ለመገበር ተገደዱ። ይህን ጦርነት ስልጤዎች ‘ያንሰንበት አማረ’ (የቅዳሜው

ወረራ) ብለው ይጠሩታል። በጦርነቱም ጤም ለዝቦ ጨነቆ በመባል

የሚታወቁት የስልጤ ገራድ ተሰዉ። በመሪያቸው መሞት የተነሣ ስልጤዎች

መሸነፋቸውን አምነው ለምኒልክ ገበሩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስልጤ የሸዋ

ግዛት አንዱ አካል ሆነ። ገራዳዊውም የስልጤ ሥርዓት ተደምስሶ ባለባታዊው

የአጼዎች አገዛዝ በቦታው ተተካ።በወቅቱም እንዲህ ተብሎ ተገጥሞ ነበር፤

ጎበነ ያማድ፥

ደሌ ተላማርድ፥

ገበብኝ ባሮት።

ዪሊሎይ ሸአብዶ፥

በፋፍ ቀልብ ኤለ እንዶ፥

ዶንደ አግሬን እንዶ፥

ጎቤን በጉማይዶ።

አንሰበተይ ቅለ፥

እመጫን ሚሽ አለ፥

ባራሀ ክተ ብለ፥

ዩርባታሀ ባለሀ አለ።

አማረ የወንበር፥

ገባን የቦለት በር።

ፋፈው ኤጋሀ ክንብል፥

አራስ ጩሎሽ ተንቀል፥

አራሽ ኡርፈከ የንቀል።

ትርጉሙም፤

(ራስ) ጎበና ለጥጋቡ፥

ወገቤን ሳልታጠቅ (ሳልዘጋጅ)፥

በማታ መጣብኝ (ወረረኝ)።

ሼህ አብዶ ኢሊሌ (የሰው ስም)፥

ጀግና አእምሮ የለውምን?

ጥላ ጋሻ ሆኖ ነው ጎበናን በጉማጅ የገጠሙት።

(ሼህ አብዶ በዚያን ጊዜ በጀግንነት ከተዋጉት አንዱ ነበሩ)

ቅዳሜ ጎህ ሲቀድ፥

የሚመጣ ሰው አለ፥

ምሳህን በደንብ ብላ፥

ስለእራትህ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው።

አማራ ለሥልጣን
‘ቦለት በር’ (የቦታ ስም) ገብቷል።

ጀግና እባክህን መክት፥

አራስ ልጇን ታንሳ፥

ገበሬም እርፉን ያንሳ።

ስልጤ በምኒልክ ጦር ከተሸነፈ በኋላ ብዙ በደል ተፈጽሞበታል፤ ሀብቱ

ተዘርፏል፥ ገራዱ ተገድሏል፥ መሬቱም ተነጥቆ ለጭሰኝነት ተዳርጓል።

ነገር ግን የትግሬው አጼ ዮሐንስ በወሎ ሙስሊሞች ከፈጸሙት የጭካኔ

ድርጊት ጋር ሲነፃፀር የምኒልኩ ሻል ያለ ነበር። በዘመኑ ብዙ የወሎ

ሙስሊሞች ወደ ስልጤ (ይህም ለእስሊምና መጠናከር በተጨማሪነት

አገልግሏል) አገር በስደት መጥተው ነበር።

አምደ ጽዮን እንዳደረጉት ሁሉ ምኒልክም ሕዝቡን በዐይነ ቁራኛ የሚጠብቁ

ነፍጠኞችን በስልጤ ምድር ላይ አሰፈሩ። ስልጤዎችን የጐዳው ሌላው ነገር

ደግሞ የምኒልክ ጦር ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ የሚያደርገው ዘመቻ ሁሉ

በስልጤ በኩል አልፎ ይደረግ ስለነበር ጦሩ ሲዘምትም ሆነ ከዘመቻ ሲመለስ

ይፈጽም የነበረው ዘረፋ ሕዝቡን ለከፋ ችግር ዳረገው።

........ይቀጥላል..........

#ምንጭ---------መህማቾት ከሚለው መፅሃፍ የተወሰደ

     ዋቢ- መጽሐፍት

1. Survey of Ethiopia and The Horn II, Addis Ababa University.

2. ፈድሉ ኑር፥ የስልጤና አዘርነት–በርበሬ ተረትና ምሳሌ፥ 1964

(ለመመረቂያ ያዘጋጁት)።

3. ዶክተር ላጵሶ ግ. ድሌቦ፥ የኢትዮጵያ ረጅም የሕዝብና የመንግሥት

ታሪክ፥ አዲስ አበባ፥ 1982።

4. Mengesha Rikitu, Oromo Oral Treasvre, June 1992, London,

England.

5. ዶክተር አብርሃም ሁሴንና ሀብታሙ ወንድሙ፥ ያዘርነት በርበሬ ባህልና

ታሪክ፥ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት።

6. William A. Shack; The Gurage, Oxford University Press, 1966.

7. ሁሴንና አወል፥ 'ጎባ' (የስልጥኛ የጀግና ግጥሞች፤ ያልታተመ)።

8. ጎጎት (በጉራጌ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ የተዘጋጀ)፥ 1987፥

ወልቂጤ።

9. ኤባ ጉት፤ ሁሴን መሐመድ፥ የስልጥኛ–አማርኛ–መዝገበ ቃላት፥ 1988።

10. ወርቁ ንዳ፥ ጀብዱ፥ አዲስ አበባ፥ 1983።

11. ዶክተር አብዱረህማን መሀመድ ቆራም፤ ማኽማኽ (የሐረሪ ተረትና

ምሳሌ)፥ መጋቢት 1984፥ አዲስ አበባ።

12. ሁሴንና አወል፥ 'የስልጤ ወጋ–ወግ' (የስልጤ ወግና ታሪክ፤ ያልታተመ)።

13. ዶክተር አብዱረህማን መሀመድ ቆራም፤ ጩቅቲ ክታብ (ሐረሪ–አማርኛ

መዝገበ ቃላት)፥ አዲስ አበባ፥ 1984።

14. የስልጤ ተውፊት

Monday, December 17, 2018

የስልጤ ኡመት አዝጋጋሃ አሊቀ ቡርዳና አሊቀ

በባቴ ባድ አዝጋግ የተለቀ ተምበከሰ ሚካትከ ሉልም አዝጋግ ይተርፋን፡፡
ሊኢቀደ በሶማሌ ቀፈት በነቀይ ተምበከሰ መጪንትኒሙ ስልጤ ዮኑ ቡርኩት ስብቸ ተደወሶን በላምኒሙ ቡርደኒሙዋ ዲነተኒሙ ሀደጎኔ ተሰደዶ ስልጤ ዞን ገቦኒ ዞኒ ባባቤዤኒሙ ወክትለኜ ኤት አፉሎትኒሙ ይቻላን።
ባውጄይ አያምንገ በሞያሌ በነቀይ ተምበከሰ መሰ ህልቂኒሙ ቀሊን አይብሌን ሰብቸ አላውራይ ዌጄኒሙ ኤንዞኔ አፌጀሮ የስልጤ ዞን ቡር ከተመ ወራቤን ገቦ ቡርዥ ቡርዥ ቲሉ ረከብነይማን።
ቀለም ተይቄሪ የዞን መትንዳደሬ ተሰደዶ የመጡይ ሰብቸ ክሼኒሙ ተጋር አበሮስኒሙ ተደበሎት የሆንኮ በጀረቦት የሰጌኒሙ ይገቦነኮ አሼኜይማን።
በለወክተ ዮገሬተይ ወደልነት ይጀረቡያነይ ዮገሬት ቂባጨ ያጄጂያነይ ደውሰ ቲጀረቢን ደውሲ ተምጦትከ ቀደ ወገሬተን ይትቄብጦን ጊስቻን በሰአዝጋግነ አትቂዲሞኔ ተቅራቀሮት ይትጌባናን የላነይ ያያሚ ሉክትነ፡፡