#መህማቾት_መሮሼ_ዚጠኜ
1) ሂመይ ታለ ወይ ባለ ደረሳይ።
2) ሁልም ግዝ ያቆምሳነይ ተፈይነትን።
3) ሁል ወለበ፥ ላመ ማ አለበ።
4) ለመጥከ እረውጣን ሰበ እቀድመያን ኤለ።
5) ገዋነ የሼዙይ ግነ አተ በሄ ምነ ጠቀልካሀ እላን።
6) ገደሞ የሰረርትም ለሰረርት በደችመ ትቃናት።
7) ገገ አቴነሴ ስሀረ ተስኮት ገገ አኬረሴ ጤብሰ እንደሮት እጠቅላን።
8) ገገከ ለላቀተለ አቴሀማት፥ ተዞፍከ ኤማት።
9) ለቄነጡኝ አዘር ደም ወጣኝ ባት ባሊ።
10) ገንደ በደል ዬለ በደል ታገቤሽ ባለ ማረቆ።
‘ገንዳ’ በሆድ የሌለን በሆድ ታገቢያለሽ (አለ ማረቆ)። (ማረቆዎች ስልጤን ገንዳ
ብለው ይጠሩታል፤ እንድንጠራጠር አደረጋችሁ ለማለት ነው።)
11) ለደልዋ ሎልድ የከሼ ግዘ ሁለ እሎቡይ።
12) ዱዱቆ፥ ነይ ሞቆ።
13) ለዱሬሸ ብቼ፥ ዜገ ተጎነኔከ በቼ፥
14) ለዱንየ ተዮን ላያንዋ ለበረከ የብኪ።
15) ዶንቀ ምሽት ያለይ ሚሽ ባብሌ እላመሽ።
16) ጀማሽ ያላን በለ፥ ሳፍራሽ ቀልቀለ።
17) ጅረዋ አማቺ በሩቅን ፈየ
18) ለጭልማይ ኑር፥ ለምካትሚ መለ ያትኬሺማን።
19) ዱሬሻም ዜጋም ቅጦም እበኮን።
20) ሀብታምም ድኻም እኩል ያለቅሳሉ።
21) ዱበን ባለቢ ኤት አመረዋ ወራበ እለትቀበጥ።
22) ዱንየ ላማድ፥ ኡምር ለተውበት።
23) ሊመርጥ የመጠ ቢጦቅሱይ እለትመረር
24) ሊሌቀ የላለቀይ (ወልድ) ባራስ ጋር እሲቃን።
25) ሊልጦፍ ትሎን እመሽብኛን፥ ሊልሞት ትሎን እሶጅብኛን ባት ኡማርቴ።
#በሂልቅ ምስት ደር ያለይ መህማቾት ወድድኩሙይ
Wednesday, February 27, 2019
መህማቾት
Sunday, February 3, 2019
አሁኑኑ ተገባራዊ የማደረገ ልምድን ማዳበር
#አሁኑኑ ተገባራዊ የማደረገ ልምድን ማዳበር
“እስከ ጨረቃ ውልደት ድረስ ይተኛል ቀን በፀሀይዋ ሙቀት ሲዝናና ይውላል፣ ኑሮውን በሙሉ "ነገ፡እሠራዋለሁ" ሲል ያሳልፈዋል፣ ምንም ነገር ሳይሠራም ይሞታል፡፡'
ጀምስ ስስበሪ
ሁላችንም ብንሆን አንድን ነገር ላለመሥራት ስንፈልግ ሌላ ጊዜ አንሠራዋለን ብለን የማዘግየት ልማድ አለን፡፡ ቢያንስ እኔ አንዲህ ዓይነቱ ልምድ እንዳለኝና ብዙ ጊዜ በኋላ ላይ እንደምፀፀትበት አውቃለሁ። ነገሮችን ማዘግየት መጥፎ ወደሆኑ አስተሳሰቦች ይመራናል፡፡ ነገሮችን ማዝግየቱ ከመሥራቱ የባሰ ውስብስብ ስሜት ውስጥ ይክተናል፡፡
#የተጠናቀቀ ሥራ እርካታና ኃይልን የሚያጐናጽፍ ሲሆን ያልተጠናቀቀ ሥራ ግን ኃይልን ይመጥጣል! እርካታም ያሳጣል፡፡
#በጐ አመለካከትን ለማዳበር ፍላጐት ካለን ዕቅዶቻችንን መጠናቀቅ በሚገባቸው በተገቢው ጊዜ እያጠናቀቅን ሕይወትን ዛሬን ብቻ
አንደምንኖራት አድርገን አንኑራት፡
“ትልቅ ልጅ ስሆን ይህንንና ያንን አደርጋለሁ”. . . ብሎ በህፃንነቱ ዕቅድ ያወጣ አንድ ሰውዬ ነበር፡፥ ትልቅ ልጅ ሲሆን ደስተኝነት የሚሰማው የኮሌጅ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ እንደሆነ ተናገረ፡ የኮሌጅ ትምህርቱን አንዳጠናቀቀ ደግሞ የመጀመሪያውን ሥራ እስካላገኘ ድረስ ደስታ አንደማይሰማው ሲናገር ተደመጠ። ሥራ በያዘበት ቅፅበት ትዳር ካልያዘ
በቀር እንዴት ደስተኛ እንደሚሆን እንቆቅልሽ እንደሆነበት አወጋ። ትዳር አንደያዘ ደግሞ ልጆቹ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ከማየት የበለጠ ደስታ
እንደማይኖር መናገሩን ሰዎች ሰሙ፡። ልጆቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ደስታ የሚያገኘው ጡረታ በወጣበት ቀን እንደሚሆን ተነበየ፡፡
ጡረታ የወጣ ጌዜስ ምን ይታየው ይሆን?
አንዳንድ ሰዎች ነገሮችን የማዘግየት መጥፎ ልምዳቸውን ኃይለኛና ጥልቅ በሆኑ ቃላት ጀርባ ሸሸገው ያዳብሩታል
ለምሳሌ "ጥናት እያደረኩበት ነው" በማለት ድክመታቸውን በውብ ቃል ይሸሽጉታል፡፡ እነኚህ
ሰዎች ያልተረዱት ነገር ቢኖር በጥናት ተቀፅላ የመሆን በሽታ እየተሰቃዩ እንደሆነ ነው፡፡
ሌላም "“አየተዘጋጀሁበት ነው!" የሚል ዓይነት አባባል ኣለላችሁ፡፡
ከአንድ ወር በኋላም እየተዘጋጀ ነው፡፡ ስድስት ወራት ካለፉ በኋላም ምላሹ
ያው "እየተዘጋጀሁ ነው” የሚል ነው፡ ታድያ እኚህ ሰዎች “ሰበብ የመፍጠር” በሽታ ሰለባ እንደሆኑ ሰው ካልነገራቸው በምን ማወቅ ይችላሉ?
ሕይወትኮ የምትገዙትን ልብስ አንደ መሞከር ዓይነት አይደለችም፡፡ ስለ ሕይወት የፈለጋችሁን ፍልስፍና ብትክከተሉም ከዚህ "ሕይወት" በተሰኘው ጨዋታ ውስጥ ያለን ዕድል አንድና በድጋሚ የማይገኝ ስለመሆኑ አትከራከሩም፡፡ ያንን ዕድል ማባከን የሚፈጥረው መዘዝ አከባድና አስከ ቀጣዩ
ትውልድም ሊጓዝ የሚችል ነው፡፡
አሁን ስንት ሰዓት ነው? የት ነው ያለነው? ለሚሉት ሁለት ጥያቄዎች ምላሾቹ አሁን እና አዚህ የሚሉት ቃላት ናቸው፡፥
ስለዚህ አሁኑኑ ያለንበትን ሁኔታ ምርጥና በጐ በማድረጉ ላይ እንትጋ በነገራችን ላይ ስለ ወደፊቱ ማሰብ የለብንም እያልኩኝ አይደለም፡፡ ግን የአሁኑን
ጊዜያችንን ምርጥ ካደረግነው ለቀጣዩ ሕይወታችን ምርጥ ዘር እየዘራን ነው ማለት ይቻላል፡፡
በጐ አመለካከትን የማዳበር ፅኑ ፍላጐት ካለን ነገሮችን በይደር የማዘግየት ልምዳችንን እርግፍ አድርገን በመተው "አሁኑኑ የመሥራት" ልምድ ማዳበር ይጠበቅብናል
#በሕይወት ውስጥ የመጨረሻዎቹ አሳዛኝ ንግግሮች፡-
"ቢሆን ኖሮ. . "
“ባላደርገው ኖሮ. . ."
“ላደርገው እችል ነበር. . "
"ባደርገው ጥሩ ነበር. . '"
“ትንሽ ጠንቀቅ የማለቱን ዕድል አግኝቼው ቢሆን ኖሮ. . ."
“ዛሬ ልትሰራው የምትችለወን በፍፁም ለነገ አታሳድረው"
ቤንጃሚን ፍራንክሊን
እርግጠኛ ነኝ ሁሉም አሸናፊዎች ነገሮችን ለነገ ማስተላለፍ ይገደዱ ነበር፡፡ ግን በፍጹም ለዚያ ስንፍና አልተንበረከኩም፡፡
ሰዎች "ከሚቀጥሉት ቀናቶች ውስጥ ባንዱ አደርገዋለሁ" ሲሉ ከሰማችሁ በፍፁም አንደማያደርጉት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ፡
አንዳንድ ሰዎች ገና ከቤት ሳይወጡ መንገዱ ላይ ያሉት መብራቶች በሙሉ አረንጓዴ እንዲሆኑላቸው ይፊልጋሉ፡፡ ያ ደግሞ የሚሆን አይደለምና
ገና ሳይጀምሩት ተሸናፊ ይሆናሉ፡፡ ተሸናፊነታቸው ገና ከመነሻው ላይ ነው፡
“ሌላ ጊዜ አደርገዋለሁ” ማለትን አቁሙ፤ ነገሮችን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍን የምናቆምበት ትክክለኛው ወቅት አሁን ነው።
ለአሸናፊነት መገዛት ከሚለው
መፅሃፍ የተወሰደ